Showing posts with label Amharic News. Show all posts
Showing posts with label Amharic News. Show all posts

Wednesday, April 27, 2016

ዜጎች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መፍለሳቸውን ቀጥለዋል


ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙና በምእራባውያን የአኗኗር ዘዴ የሚኖሩ ጥቂት ግለሰቦች የመኖራቸውን ያክል፣ ተገኘ የሚባለው የኢኮኖሚ እድገት የዘለላቸው ወይም ፈጽሞ ያላያቸው እጅግ በርካታ ዜጎች ስደትን እንደአማራጭ በመውሰድ ባህር እና በረሃ አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ወይም ወደ አውሮፓና አሜሪካ ሲሰደዱ ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ጉልበቱ የሌላቸው አቅመ ደካሞች ደግሞ ወደ ዋና ዋና የክልል ከተሞች ተሰደው በልመና ህይወታቸውን በመግፋት ላይ ናቸው። ብዙውን ጊዜ የከተሞችን ገጽታ ያበላሻሉ፣ የልማታዊ መንግስቱን ስም ያጎድፋሉ በሚል ከከተሞች እየታፈሱ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እየተወሰዱ ይጣላሉ። በተለይ ከ20 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች በርሃብ መጠቃታቸውን ተከትሎ፣ የቻሉት ወደ ከተሞች ተሰደው ችግሩን ለማሳለፍ ቢሞክሩም ፣ በመንግስት ካድሬዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል። ቀያቸውን ለቀው እንዳይሄዱም፣ በጸጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል።
በአዲስ አበባ ውስጥ በተናጠል የሚመጡና በልመና ላይ የተሰማሩ ዜጎችን ሁሉንም የእድሜ ክልልና ጾታዎች የሚያካትት ነው። የኢሳት ካነጋገራቸው ዜጎች ለመረዳት እንደሚቻለው ብዙዎቹ ተሰደው የመጡት ከአማራ ክልል ነው።
በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ነዋሪ የሆኑና በአዲስ አበባ በልመና ህይወታቸውን ለማቆየት የሚጥሩት እናት እንደተናገሩት፣ በአካባቢያቸው የገባው ረሃብ ከፍተኛ በመሆኑ በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። መንግስት በቂ እርዳታ ለመስጠት ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት መገደዳቸውን ገልጸዋል
ከአዊ ዞን እንደመጡ የተናገሩት ሌላ እናት በበኩላቸው፣ ችግሩ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ፣ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለመለመን መገደዳቸውን ተናግረዋል።
የማዳበሪያ እዳ አስመርሯቸው መምጣታቸውን የሚናገሩት አንድ አዛውንት፣ ለምነው በሚያገኙት ገንዘብ እዳቸውን ለመክፈል ማሰባቸውን ይገልጻሉ
የሚጦሩዋቸው ልጆች በማጣታቸው ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ የሚናገሩ ሌላ አዛውንት፣ በአዲስ አበባ ህዝቡ ምጽዋት እየሰጠ እያኖራቸው መሆኑን ተናግረዋል

የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ ተብለው በመንግስት ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ኩባንያዎች ውጤታማ አይደሉም ተባሉ


ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008)
የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኙ ታስበው በመንግስት ልዩ የማበረታቻ ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ከ30 በላይ ኩባንያዎች በየወሩ ስድስት ሚሊዮን ዶላር እንዲያስገኙ ቢጠበቅባቸውም ከ90 ሺ ዶላር በታች ማስመዝገባቸው ተገለጠ።
በጉዳዩ ቅሬታ የተሰማቸው የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ድርጅቶቹ ሲደረግላቸው የቆየ ልዩ ልዩ ድጋፍ ተቋርጦ በኩባንያዎቹ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ አሳስበዋል።
እነዚሁ በብረታ-ብረትና በኤሌክትሮኒክስ ማምረት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ድርጅቶች ለምርት ግብዓት የሚሆናቸውን ጥሬ እቃ ያለቀረጥ ወደሃገር ውስጥ እንዲያስገቡና ሌሎችም ድጋፎች ሲደረጉላቸው መቆየቱን የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።
ይሁንና መንግስት ከኩባንያዎቹ አገኘዋለሁ ብሎ ሲጠብቅ የነበረ የውጭ ምንዛሪ አለመገኘቱንና ድርጊቱ በሃገሪቱ የፋይናንስ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳሰሩም ተገልጿል።
ወደ 35 የሚደርሱ ኩባንያዎች በየወሩ በአማካይ ስድስት ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ያስገኛሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከ90ሺ ዶላር በታች ማስገባታቸውን የኢንስቲትዩቱ ባለስልጣናት ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
የገበያ እጦት እንዳጋጠማቸው አስታውቀዋል የተባሉት ድርጅቶች ምርታቸውን ለሃገር ውስጥ ገበያ በማቅረባቸው ምክንያት መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንዳጣ መንግስታዊው ኢንስቲትዩት አመልክቷል።
የኢትዮጵያ የውጭ ገቢ ንግድ እያሽቆለቆለ መምጣትን ተከትሎ መንግስት በዘርፉ በተሰማሩ የንግድ ተቋማት ላይ ምርመራን እያካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የእርሻ ስራዎች ለውጭ ባለሃብቶች የተሰጡ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችም በመንግስት ላይ ኪሳራ መስከተላቸው ይታወቃል።
በተለይ የውጭ ምንዛሪን ያስገኛሉ ተብሎ ልዩ ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ኩባንያዎች ሊያመጡ ከታሰበው ጥቅም ይልቅ ኣያደረሱ ያለው ኪሳራ ከፍተኛ መሆኑንም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተለያዩ ክልሎች ለውጭ ኩባንያዎች በልዩ ድጋፍ ሲሰጥ በቆየው ሰፋፊ የእርሻ መሬት ላይ በብድር የተሰጠ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የገባበት አለመታወቁን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ለጥጥ ምርት በተሰጠ የእርሻ መሬት ላይ ተመሳሳይ ኪሳራ ያጋጠመ ሲሆን፣ ሃገሪቱ የጥጥ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የያዘችው እቅድ ሳይሳካ መቅረቱንም የመንግስት ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርገዋል።

Tuesday, April 26, 2016

ሃረር ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ተወጥራ ዋለች


ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ 2 ሺ በላይ ቤቶችን ለማፍረስ በዝግጅት ጋር ያለው የክልሉ መንግስት፣ ዛሬ ከህዝብ ጋር ተፋጦ መዋሉን ወኪላችን ገልጿል። ህዝቡ “ከ10 አመታት በፊት ቤቶችን ስንሰራ ዝም ብላችሁ አሁን ለምን እርምጃ ለመውሰድ ተነሳችሁ? በክረምት ቤተሰቦቻችንን ሜዳ ላይ መበተን ሰብአዊነት ነው ወይ? ለምን ቤቶቹን ህጋዊ አታደርጉልንም?” የሚሉ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ የቆዬ ቢሆንም፣ መልስ ሊያገኝ አልቻለም።
በሸንኮር መስተዳደር ስር በሚገኙ አካባቢዎች 1 ሺ ያላነሱ ቤቶች እንደሚፈርሱ የገለጸው ወኪላችን ፣ ዛሬ ሸንኮር መስተዳድራና በድሬ ጥያራ መለያ ቦታ ላይ በሚገኘው ድልድይ ላይ ነዋሪዎች ቋጥኝ ድንጋይ እያንከባለሉ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን፣ ይህን አልፎ በሚመጣ ላይ እርምጃ እንወስዳለን በማለት በመናገር ላይ ናቸው።
ቤቶቹ የሚፈርሱት በሸንኮር ወረዳ፣ ከአቡበክር ወረዳ፣ ከሃኪም ወረዳ እንዲሁም ከሶፊ ወረዳ ናቸው። ጊዮርጊስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ቤት አፍራሽ ግብረሃይል ቤት ማፍረስ የጀመረ ሲሆን፣ ህዝቡ ቀኑን ሙሉ በጩከት ተቃውሞውን ሲገልጽ ውሎአል። አንድ አዛውንት የጎረቤታቸው ቤት ሲፈርስ አይተው በድንጋጤ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
ቤቶቻቸው የሚፈርሱባቸው ሰዎች በየአመቱ ግብር ይገብሩ እንደነበር ነዋሪዎች በማነጋገር ወኪላችን ከላከው መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

Monday, April 11, 2016

በአፋርና በኢሳ ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ



በአፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ በአፋርና በኢሳ ሶማሊ ጎሳዎች መካከ ግጭት ተቀስቅሶ በግንሹ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ሰዎችም ለጉዳት መዳረጋቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሰኞ ገለጠ።
በወረዳው አስጊታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት አንድ የአፋር ተወላጅ ወጣት በኢሳ ሶማሊ ጎሳ መገደሉ ተከትሎ እንደሆነ የድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ገሃስ መሃመድ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።
በአካባቢው ሰኞ ምሽት ድረስ የተኩስ ልውውጥ በመካሄድ ላይ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሎ ስጋት መኖሩን ሃላፊው አስታውቋል።
በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ለዘመናት ሲቀርቡ የነበሩ አስተዳደራዊ ጥያቄዎች እልባት ባለማግኘታቸው ምክንያት በወረዳው ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝም የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃጎስ መሃመድ ተናግረዋል።
ሁለቱ ጎሳዎች እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከግጦሽ መሬት ጋር በተገናኘ በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ይገቡ እንደነበር ያወሱት ሃላፊው በአካባቢው መነሳት የጀመሩ አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ጉዳዩ በሚመለከታቸው የመንግስት ሃላፊዎች በኩል ችላ መባላቸው ሳቢያ ግጭቱ በአዲስ መልክ መቀጠሉን አስረድተዋል።
በዚሁ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ውጥረት አፋጣኝ እልባትን ካላገኘም ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰታቸው እንደማይቀር የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አክሎ አመልክቷል።

Wednesday, April 6, 2016

በህገወጥ ንግድ ተሰማርታችኋል የተባሉ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ


ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008)
በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርታችኋል የተባሉ 120 ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባለፉት 30 ቀናት ብቻ በቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚሁ ነጋዴዎች ያለ-ደረሰኝ ግብይትን ሲፈጽሙ ቆየተዋል ሲል ረቡዕ አስታውቋል።
ባለስልጣኑ 85 አምራቾች፣ አስመጪዎችና የጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ ድንገተኛ ዘመቻ ማካሄዱን አውስቶ ከ85ቱ የንግድ ድርጅቶች መካከል 77 የሚሆኑት ያለ-ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ መገኘታቸውን ይፋ እንዳደረገ ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጀ ለመረዳት ተችሏል።
ባለስልጣኑ ነጋዴዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢገልጽም ክስ ይመስርት አይመስርት ግን ያስታወቀው ነገር የለም።
በዚሁ ድንገተኛ ዘመቻ ክትትል ከተደረባቸው መካከል 90 በመቶ የሚሆኑ በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውን ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ባለስልጣኑ አክሎ ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ በርካታ ነጋዴዎችና ባለስልጣናት በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

ድርቅ የተባባሰባቸው 438 ወረዳዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው ተባለ


ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008)
በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ችግሩ የተባባሰባቸው ወረዳዎች 438 መሆናቸው ተገለጠ። የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሰሞኑን ለመንግስት አካላት ባሰራጨውና “አስቸኳይ” በሚል በበተነው ማሳሰቢያ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ድርቁ የተከሰተ ሲሆን፣ በአንዳንድ ወረዳዎች ደግሞ ይበልጥ አሳሳቢ ሆኖ ተገኝቷል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም በጉዳዩ ዙሪያ ሰፋ ያለ ሪፖርት ያወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን፣ በውስጥ በኩል ባሰራጨው መረጃ መሰረት 100 ያህል ወረዳዎች ክፉኛ ተጠቅተዋል።
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ለሚመለከታቸው አካላት ባለፈው ሳምንት ባሰራጨው ሪፖርት በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁ 438ቱ ወረዳዎች 123ቱ በኦሮሚያ ክልል ሲሆኑ፣ በአማራ ክልል 80 ፥ በደቡብ 72 ፥ በሶማሊ ክልል 63 ፥ ወረዳዎች በተመሳሳይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአፋር ክልል በ32 ወረዳዎች፣ በትግራይ 31 ወረዳዎች፣ በጋምቤላ 13 ወረዳዎች በቤኒሻንጉል 9 ፥ በሃረር 2 ፥ እንዲሁም በድሬደዋ አንድ ወረዳ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅተዋል።
በድርቅ ክፉኛ ከተጠቁት 438 ወረዳዎች 85 ያህሉ ወረዳዎች ደግሞ ይበልጥ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተመልክቷል። በተለይ  በአፋር ድርቁ የተከሰተባቸው 32 ወረዳዎች ሁሉም አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መገኘታቸው ይፋ ሆኗል። በኦሮሚያ ከ123ቱ ወረዳዎች 52ቱ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሲሆኑ፣ በአማራ ክልል ከ80 ተጠቂ ወረዳዎች 38ቱ ላይ የተባባሰ መሆኑም መደረጉ ተችሏል።
በትግራይም በድርቁ ክፉኛ የተጠቁ 31 ወረዳዎች 20ዎቹ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውም ይፋ ሆኗል። በሶማሊ ክልል ክፉኛ ከተጠቁት 63 ወረዳዎች 24ቱ ይበልጥ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሲገለጽ፣ በደቡብ  ክልል ከተጠቁት 72 ወረዳዎች 17ቱ ይበልጥ የከፋ ሁኔታ ውስጥ መገኘታቸውንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰንጠረዥ አስደግፎ በውስጥ ካሰራቸው መረጃ መረዳት ተችሏል።

በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ብቻ የትግራይ ህዝብ ተጋድሎ ለሚያሳየው ፊልምና መጽሃፍ ገንዘብ እንዲያዋጡ ተጠየቁ


ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008)
በሃገር መካላከያ ሰራዊት ውስጥ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ለብቻቸው እየተጠሩ ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸው የመከላከያ ሚኒስቴር ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በሁሉም የጦር ክፍሎች እንዲካሄድ ከበላይ ወረደ በተባለ ትዕዛዝ መሰረት በዚሁ ሳምንት በሁመራ ግንባር ስብሰባው መካሄዱንም መረዳት ተችሏል።
በሁመራ ግንባር በሚገኘው 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ውስጥ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ለብቻቸው ተጠርተው፣ የትግራይን ህዝብ ተጋድሎ የሚያሳየው ፊልምና መጽሃፍ ገንዘብ እንዲያዋጡ ተጠይቀዋል።
በስብሰባው ውስጥ የነበሩት አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ለብቻቸው የተደረገላቸውን ጥሪ የተቃወሙ ሲሆን የሌላው ኢትዮጵያዊ ተጋድሎስ በማለት መጠየቃቸው ተመልክቷል።
ከሰራዊቱ አባላት ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ መስጠት የተሳናቸው የስብሰባው መሪዎች፣ የበላይ አካል ትዕዛዝ ስለሆነ እኛ መለወጥ አንችልም በማለት ማሰናበታቸውም ተመልክቷል።
የትግራይ ህዝብ ተጋድሎ ያሳያል የተባለው ፊልም እንዲሁም መጽሃፍ በማን እንደተዘጋጀና መቼ ለእይታ እንደሚበቃ የታወቀ ነገር የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የበታች ሹማምንትና መኮንኖች ያሳተፈ ስብሰባ በሁሉም የጦር ክፍሎች እንዳካሄደ ከበላይ አካል ትዕዛዝ መወርዱ ታዉቋል። በሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ለመወያየት በሚል የተዘጋጀው ስብሰባ በአንዳንድ ጦር ክፍሎች ቀደም ሲል የተጀመረ ሲሆን፣ በሌሎችም  እንደሚቀጥል የመከላከያ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።

የድምጽና ምስል ግንኙነት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል እየተመከረበት እንድሆነ ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ


ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008)
ቫይበርና ሌሎች የስልክ ጥሪ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያን ለመጣል አሊያም ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ኢትዮ-ቴለኮም እየመከረ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዱአለም አድማሴ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።
አገልግሎቱን የመቆጣጠር ቴክኖሎጂ እንዳለው የገለጸው ድርጅቱ ከአገልግሎቱ ባለቤቶች ጋር በመደራደር አመታዊ የትርፍ ድርሻቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ መግባባት እንደሚቻልም አመልክቷል።
በአገልግልቶቹ መስፋፋት ከፍተኛ ገቢን እያጣ እንደሆነ የሚገልጸው ኢትዮ-ቴሌኮም አማራጮችን በማየት የተሻለውን ለመጠቀም ምክክር እየተካሄደ እንደሆነም ይፋ አድርጓል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው አዲስ ሊጣል የታሰበው ክፍያ አገልግሎቱን እንዳይጠቀሙ የሚያደርግ እንደሆነና የስልክ ቁጥሮች ምዝገባውም ቁጥጥር ለማጥበቅ የታሰበ ነው ሲሉ በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ በኢንተርኔትና በስልክ አገልግልቶች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥርን የምታደርግ ሃገር መሆኗን የተለያዩ አካላት ሲገልፁ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ተግባራዊ ሊደረግ የታሰበውም አዲሱ ቁጥጥር ይህንኑ ድርጊት የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል።

Sunday, January 17, 2016

በሰርጉ ዋዜማ በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቀዶ ጥገና ተደረገለት


ኢሳት (ታህሳስ 5 2008)

በኢሊባቡር መቱ በሰርጉ ዋዜማ በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ ህይወቱ አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ አመለከተ።

ታህሳስ 29 ቀን 2008 ዓ ም ጭንቅላቱን በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም፣ በመቱ ሆስፒታል ከታየ በኋላ ለከፍተኛ ቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከዚያም ወደ ወደአለርት ሆስፒታል ተልኮ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ወደ ጥቁር አንበሳ ተመልሶ ቀዶ ጥገና እንደተደረገለት ለማወቅ ተችሏል።

በጥቁር አንበሳ በዛሬው እለት ቀዶ ጥገና የተደረገለት ፍጹም አባተ፣ የማየት እድሉ ከ 5-10 ፐርሰንት እንደሆነ ቀዶ ጥገናውን ያደረጉ ሃኪሞች መናገራቸው ታውቋል።

ጭቅላቱን በጆሮ በኩል በኋላ የተመታው መምህር ፍጹም፣ ቀዶ ጥገና ከተደረገለት በኋላም ቢሆን ብዙ መናገር እንደማይችል ቤተሰቦቹ ለኢሳት አስረድተዋል።

በሙሽራው ላይ የተኮሱት የመንግስት ወታደሮችም በህግ ቁጥጥር ስር ላይ ናቸው እንደተባሉ የሙሽራው አባት አቶ አባተ ለኢሳት ገልጸዋል። ወታደሮችም ለምን ይህንን አይነት የጭካኔ እርምጃ እንደወሰዱ የሚታወቅ ነገር የለም ተብሏል።

የቤተሰቡ ሶስተኛ ልጅ የሆነውና ለ8 ዓመት በመምህርነት ያገለገለው ፍጹም አባተ፣ አጥንቱ ከመሰበሩም በተጨማሪ፣ ደም ወደውስጥ እንደፈሰሰበትም ወላጅ አባቱ አቶ አባተ ለኢሳት ገልጸዋል።

“በልጄ ላይ ደረሰው አደጋ በማንም ላይ እንዳይደርስ እፈልጋለሁ” ያሉት የመምህር ፍጹም አባት አቶ አባተ፣ የህክምናውን ወጪ የሚሸፍኑት በእድሜ የገፉ የፍጹም አባትና ቤተሰቦቻቸው እንደሆኑ ለኢሳት ተናግረዋል።

የመምህር ፍጹም እጮኛ ወ/ሪት ፍሬህወት በበኩሏ አደጋው እጅግ በጣም አስደንጋጭ ሁኔታ እንደፈጠረባት ለኢሳት ገልጻለች።

ሰለአደጋው በስልክ ከሙሽራው እህት እንደተደወላት የተናገረችው ወ/ሪት ፍሬህወይት፣ መኪና ተፈልጎ ከበቹ ወደ ቡሪሳ ሌሊት እንደመጣችና ተጎጂ እጮኛዋን ማየት እንደቻለች አስረድታለች።

ወ/ሪት ፍሬህይወት በለጠ የኢትዮጵያ ህዝብም ጸሎት እንዲያደርግ ጠይቃለች።

መምህር ፍጹም፣ በስራው እጅግ የተከበረና በተማሪዎች ዘንድም በጣም ተወዳጅ እንደሆነ የተለያዩ ሰዎች መስክረዋል።

Source:: Ethsat

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው


ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008)

በኦሮሚያ ክልል ዳግሞ ቀጥሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ አርብ በምስራቅ ሃረርጌ እንዲሁም በምዕራብ ሸዋ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲካሄድ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።

በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችና ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን እርምጃ በማውገዝ የተቃውሞ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን ታዉቋል።

ይሁንና የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን በወሰዱት እርምጃ በርካታ ተማሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞም በምዕራብ ወለጋ አካባቢ መካሄዱን ለመረዳት ተችሏል።

የአምቦ ዩንቨርስቲን ጨምሮ በዲላና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ማስተማሩ ሂደት አሁንም እንደተቋረጠ ተማሪዎች አስታውቀዋል።

ዩንቨርስቲዎቹ ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማሳሰቢያ ቢያወጡም ትምህርት አለመጀመሩን ተማሪዎች አክለው ገልጸዋል።

ትምህርታቸውን አቋርጠው የሚገኙ ተማሪዎች ለእስር ተዳርገው የሚገኙ ተማሪዎች እንዲፈቱና የጸጥታ ሃይሎች የሚወስዱትን የሃይል እርምጃ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

በዩንቨርስቲዎቹ ሰፍረው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ለደህንነታቸው ስጋት ኣንደሆኑባቸው የሚገልጹት እነዚሁ ተማሪዎች፣ ጥያቄያቸው ምላሽ ካላገኘ ትምህርታቸውን እንደማይቀጥሉ ገልጸዋል።

Source:: Ethsat

Thursday, January 14, 2016

በአዲስ አበባ ካለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የመንገድ ዳር ንብረቶች መወረሳቸው ተዘገበ


ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ የመንገድ ባለስልጣን መስሪያ ቤት በመንገዶች ዳርቻ ያሉ ዓመታዊ ግብር ተከፍሎባቸው የቆሙ ቢልቦርድ የንግድ ማስታወቂያዎችን ለድርጅቶቹ ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጣቸው ሳይሰጣቸው ከተለጠፉበት ማንሳቱን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል። ንብረታቸው የተወሰደባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንደዚህ ዓይነት ሕገወጥ ድርጊት በሕግ ሽፋን መፈፀሙ እንዳስከፋቸው እየገለፁ ነው። የመንገድ ባለስልጣኑ በበኩሉ በሬድዮ ለሶስት ቀናት ማስታወቂያ አስነግሬያለሁ በማለት ማስተባበያ ሰጥተዋል።

Source: http://ethsat.com/amharic/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8a%ab%e1%88%88%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%88%9d-%e1%89%85%e1%8b%b5%e1%88%98-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8c%a0%e1%8a%95%e1%89%80%e1%89%82/

Thursday, January 7, 2016

ሱፊ ቱራ አዳም ይባላል። ትናንት ከሂርና ከተማ በኢህአዴግ ታጣቂዎች ታስሮ ከሌሎች ጋር ወደአዲስ አበባ እየተወሰደ ሳለ በደረሰበት ድብደባ ወታደሮች የሞተ መስሏቸው ከመኪናው ላይ ወርውረው ጥሻ ውስጥ ጣሉት።

ሱፊ ቱራ አዳም ይባላል። ትናንት ከሂርና ከተማ በኢህአዴግ ታጣቂዎች ታስሮ ከሌሎች ጋር ወደአዲስ አበባ እየተወሰደ ሳለ በደረሰበት ድብደባ ወታደሮች የሞተ መስሏቸው ከመኪናው ላይ ወርውረው ጥሻ ውስጥ ጣሉት። የአካባቢው ገበሬዎች ደርሰው ወደጭሮ ሆስፒታል ወሰዱት።


Source:https://www.facebook.com/photo.php?fbid=10207203607360555&set=a.3052522444099.2136911.1594431019&type=3&permPage=1

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መከሰቱን ነጋዴዎች ተናገሩ


ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ለኢሳት እንደገለጹት በአሁኑ ሰአት የተከሰተው የዶላር እጥረት ከምርጫ 97 በሁዋላ ከፍተኛው ነው። በአስመጭነትና ላኪነት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራቸውን ለመስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ፋብሪካዎች የመለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት በመቸገራቸው እንቅስቃሴያቸው በእጅጉ ተዳክሟል። በተለይ የግንባታ እንቅስቃሴው በእጅጉ መዳከሙን ነጋዴዎች ይገልጻሉ።
በአገሪቱ የተፈጠረውን ከፍተኛ ድርቅ ለማቋቋም መንግስት በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የእርዳታ እህል ለመግዛት ቢችልም፣ ከአለማቀፉ ማህበረሰብ የሚሰጠው ድጋፍ በመቀነሱ ተጨማሪ የእርዳታ እህል ለመግዛት አቅም አጥሮታል። ከዚህ ቀደም የተከሰተውን የዶላር እጥረት ለመቋቋም መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች 1 ቢሊዮን ዶላር ቢበደርም ፣ ሁለተኛው ዙር ብድር እስካሁን አለመለቀቁ ችግሩን አባብሶታል ሲሉ ምንጮች ይገልጻሉ።

በባህርዳር እስረኞች ለ2 ቀናት በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ተደረጉ


ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ” በእስር ቤቱ ውስጥ ቦንብ ገብቷል” የሚል መረጃ ደርሶናል በሚል እስር ቤቱን በአድማ በታኝ ፖሊሶች አጥለቅልቀውና ዋናውን መንገድ በመዝጋት ጠያቂዎች እንዳይገቡ ከልክለዋል። በዚሁ ሰበብ በእስረኞች ላይ ከፍተኛ እግልት የደረሰ ሲሆን፣ ለሁለት ቀናት ያክል እስረኞች በቤተሰቦቻቸው እንዳይጠየቁ አግደዋል። በእስር ቤቱ ውስጥም ከፍተኛ ፍተሻ ተካሂዷል።
ዛሬ ታህሳስ 28 ከቀኑ 8 ሰአት ላይ እስረኞችን ለመጠየቅ መግባት እንደተጀመረ ድንገተኛ የተኩስ ድምጽ በመሰማቱ፣ ወታደሮች ጠያቂ ቤተሰቦችን ከአካባቢው በማባረር የተወሰኑትን አግደዋል።
የተኩሱ ትክክለኛ መንስኤ እስካሁን ባይታወቅም ፣ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ፖሊስ ግን በጣና ሃይቅ በኩል ለማምለጥ የሞከረን እስረኛ ለማስቆም በሚል ተኩስ መከፈቱን ለዘጋቢያችን ተናግሯል።
በባህርዳር ዋናው እስር ቤት መንግስትን ይቃወማሉ የሚባሉ በርካታ ወጣቶች ታስረው ይገኛሉ።

በትግራይ አርሶአደሮች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 22፣ 2008 ዓም በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች ተቃውሞውን ያካሄዱት የበለስ ምርታችን በተሳሳተ ምርምር ወድሞብናል በሚል ምክንያት ነው። አርሶአደሮቹ ከዋጅራት ተነስተው በእግራቸው ወደ መቀሌ የገሰገሱ ሲሆን፣ አዲግዶም ላይ ፖሊሶች በሃይል በትነዋቸዋል።
አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ለምርምር በሚል የገባው በሽታ ፣ የበለስ ምርቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመጉዳቱ በህልውናቸው ላይ አደጋ ፈጥሯል። መንግስት በሽታውን ያመጡትን ተመራማሪዎች ለፍርድ እንዲያቀርብላቸውና አስፈላጊው ካሳ እንዲፈላቸው ይጠይቃሉ።
የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥያቄ ባቀረቡ አርሶአደሮች ላይ የሃይል እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል።

የኣብረሃ ደስታ ወንድም ታሰረ።

ዛሬ ሓሙስ 28 / 04/ 2008 ዓ/ም ለልደት በዓል ወንድማቸው ኣብራሃ ደስታ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ ማረምያቤት ያመሩ ተወልደ ደስታና ገብረሂወት ደስታ የወህኒ ቤቱ ሃላፊዎች ለገብረሂወት ኣብራሃን እንዲጠይቅ የፈቀዱለት ሲሆኑ ተወልደን ግን ይዘውት ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውታል።

ገብረሂወት ወንድሙ ኣብራሃን ጠይቆ ሲመለስ ተወልደ እንዳጣውና የት እንዳስገቡት ሲጠይቃቸው ኣናውቅም እንዳሉት ገልፆልኛል።

በነገራችን ላይ እነአብርሃ ደስታ ነገ 29/04/2008ዓ/ም ኣምስት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለብይን ይቀርባሉ።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።
It Is So.




Source: https://m.facebook.com/photo.php?fbid=964990906925899&id=100002449960026&set=a.881616671929990.1073741831.100002449960026&source=57