Thursday, January 7, 2016

በትግራይ አርሶአደሮች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 22፣ 2008 ዓም በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች ተቃውሞውን ያካሄዱት የበለስ ምርታችን በተሳሳተ ምርምር ወድሞብናል በሚል ምክንያት ነው። አርሶአደሮቹ ከዋጅራት ተነስተው በእግራቸው ወደ መቀሌ የገሰገሱ ሲሆን፣ አዲግዶም ላይ ፖሊሶች በሃይል በትነዋቸዋል።
አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ለምርምር በሚል የገባው በሽታ ፣ የበለስ ምርቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመጉዳቱ በህልውናቸው ላይ አደጋ ፈጥሯል። መንግስት በሽታውን ያመጡትን ተመራማሪዎች ለፍርድ እንዲያቀርብላቸውና አስፈላጊው ካሳ እንዲፈላቸው ይጠይቃሉ።
የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥያቄ ባቀረቡ አርሶአደሮች ላይ የሃይል እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment