Wednesday, September 30, 2015

A Summary of Oromos Killed, Beaten & Detained by TPLF Armed Forces During the 2014 Oromo Protest Against the Addis Ababa (Finfinne) Master Plan

Compiled by the National Youth Movement for Freedom and Democracy (NYMFD) (also known as Qeerroo Bilisummaa)

Background

It is a well-documented and established fact that the Oromo people in general, and Oromo students and youth in particular, have been in constant and continuous protest ever since the current TPLF led Ethiopian government came to power. The current protest which started late April 2014 on a large scale in all universities and colleges in Oromia, and also spread to several high schools and middle schools have begun as opposition to the so called “Integrated Developmental Master Plan” or simply “the Master Plan.” The “Master Plan” was a starter of the protest, not a major cause.

The major cause of the youth revolt is the opposition to the unjust rule of the Ethiopian regime in general. The main issue is that there is no justice, freedom and democracy in the country. The said Master Plan in particular would expand the current limits of the capital, Addis Ababa, or “Finfinne” as the Oromos prefer to call it, by 20 folds stretching to tens of Oromian towns surrounding the capital. The Plan is set to legalize the eviction of an estimated 2 million Oromo farmers from their ancestral land, and sell it to national and transnational investors. For the Oromo, an already oppressed and marginalised nation in that country, the incorporation of those Oromian cities into the capital Addis Ababa means once more a complete eradication of their identity, culture, and language. The official language will eventually be changed to Amharic. Essentially, it is a new form of subjugation and colonization. It was the Oromo university students who saw this danger, realized its far-reaching consequences and lit the torch of protest which eventually engulfed the whole Oromia regional state.

For the minority TPLF-led Ethiopian regime, which has been already selling large areas of land surrounding Addis Ababa even without the existence of the Master Plan, meeting the demands of the protesting Oromo students means losing 1.1 million of hectares of land which the regime planned to sell for a large sum of money. Therefore, the demand of the students and the Oromo people at large is not acceptable to the regime. It has, therefore, decided to squash the protest with its forces armed to the teeth. The regime ordered its troops to fire live ammunition to defenceless Oromo students at several places: Ambo, Gudar, Robe (Bale), Nekemte, Jimma, Haromaya, Adama, Najjo, Gulliso, Anfillo (Kellem Wollega), Gimbi, Bule Hora (University), to mention a few. Because the government denied access to any independent journalists, it is hard to know exactly how many have been killed and how many have been detained and beaten. Simply put, it is too large of a number over a large area of land to enumerate. Children as young as 11-years-old have been killed. The number of Oromos killed in Oromia during the current protest is believed to be in hundreds. Tens of thousands have been jailed, and an unknown number have been abducted and disappeared. The Human Rights League of the Horn of Africa, which has been constantly reporting the human rights abuses of the regime through informants from several parts of Oromia for over a decade, estimates the number of Oromos detained since April 2014 as high as 50,000.

In this report, we present a list, which we have managed to collect and compile, of 61 Oromos who had been killed, and 903 others who have been detained and beaten (or beaten and then detained) during and after the Oromo students protest which began in April 2014. The information we obtain so far indicates those detained are still in jail and still under torture. Figure-1 below shows the number of Oromos killed from different zones of Oromia included in this report. Figure-2 shows the number of Oromos detained and reportedly facing torture. It has to be noted that this number is only a small fraction of the widespread killings and arrests of Oromos carried out by the regime in Oromia regional state since April 2014 to date.

Source : http://gadaa.net/wp-content/uploads/2014/07/List-of-Oromos-killed-and-detained-compiled-July-05-2014-compiled-by-Qeerroo-.pdf

ሰበር ዜና ! ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ !

የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ቁጥጥር ስራ መዋሉን ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ችያለሁ ። ጋዜጠኛ ግሩም ላለፉት ሶስት ቀናት ሲታደን መቆየቱን የጠቁሙኝ ምንጮች ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠውልኛል !
የጋዘጠኛ ግሩም መታሰር እንደሰማሁ ወደ የመን ስልክ በመደዎል ያነጋገርኳት ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ በየነንየጋዜጠኛ ግሩምን መታሰር አረጋግጣልኛለች ። ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ ከዚሁ ጋር አያይዛ ጋዜጠኛ ግሩምን ያሳሰረው ኢትዮጵያዊ መሆኑንና የታሰረበትም ምክንያት ” ከተለያዩ ሃገራት በተረጅዎች ስም ገንዘብ ትሰበስባለህ ፣ ወደ ከየመን ውጭ መረጃ ታሰራጫለህ ” የሚል ክስ እንደሆነ ጠቁማኛለች ።
በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃን ከማቅረብ ባለፈ ፣ ረግተው በማያውቁት የየመን ከተሞችና በርሃ ላይ በአደጋ ተከበው ለሚሰቃዩ ስደተኛ ወገኖች በነፍስ ደራሽ የነበረው ብርቱ ጋዜጠኛ ግሩም የየመኑን የኢትዮጵያን የስደት መከራና ሰቆቃ የሚዳሰወስ “የሞት ጉዞ ” የሚል መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘመጋም !
በጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት እስራት ዙሪያ ስላሉት አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልኩ መረጃ የማቀርብ መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

Source :https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2015/09/30/dew/


Monday, September 28, 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘረኝነት እየተወነጀለ ነው

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትርፋማነቱ በተለያዩ አለማቀፍ የንግድ ተቋማት እየተመሰገነ ቢመጣም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ” ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ክሶችን እያቀረቡ ነው። አየር መንገዱ ጀምሮት ከነበረው የቁልቁለት ጉዞ የታደጉት አቶ ግርማ ዋቄ ስራቸውን ከለቀቁ በሁዋላ፣ በምትካቸው የተሾሙት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሄር ሰዎች ለማስያዝ እንቅስቃሴ መጀመራቸው፣ በትግራይ ብሄር ተወላጆችና በሌሎች ብሄር ተወላጆች መካከል ከፍተኛ የሆነ አድልዎ እየታዬ መምጣቱን እንዲሁም የህወሃት/ኢህአዴግን የፖለቲካ ፍልስፍና የማይከተሉ ኢትዮጵያውያን እድገት ይከለከላሉ፣ ከስራ ይባረራሉ ፣ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩም ይታሰራሉ።
አንዳንድ ሰራተኞች ” አየር መንገዱን ከዘረኝነት” እንታደገው በማለት በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም የሚሰማቸው አላገኙም። በዚህም የተነሳ ብዙዎቹ ሁኔታዎችን አመቻችተው ድርጅቱን እየለቀቁ ወደ አረብ አገራት፣ አውሮፓና አሜሪካ ይሰደዳሉ። አየር መንገዱ በአንጻራዊ መልክ ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ተሽሎ መገኘቱ ፣ የውስጥ ችግሩ ጎልቶ እንዳይነገር እንዳደረገው የሚገልጹት ሰራተኞች፣ በተለይ ስራ አስኪያጁ ድርጅቱን እንደ ኢፈርት ሁሉ የህወሃት ንብረት እያደረጉት ነው ይላሉ።
ሰራተኞች እንደሚገልጹት በቅርቡ የኢንፎሜሽን ክፍሉን እንደገና እናደራጃለን በሚል ቦታ ከተቀጠሩት መካከል 80 በመቶው የትግራይ ተወላጅ የህወሃት አባላት ናቸው። የአየር መንገዱ ዋና የኢንፎርሜሽን ኦፊሰር በቅርቡ በጡረታ ሲገለል፣ እሱን ተከትሎ የተቀጠረው ምህረተ አብ ተክላይ ነው። ምህረተአብ በአየር መንገዱ ስራ ከጀመረ 4 አመታት ብቻ የቆየ ቢሆነውም፣ በሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ ከ15 እስከ 25 አመታት ልምድ ላላቸው የድርጅቱ ሰራተኞች ሃላፊ ሆኖ መሾሙ ዘረኝነቱ እየከፋ መምጣቱን ማሳያ ነው በማለት ይናገራሉ። ከ4 አመታት በፊት አቶ ተወልደ የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ በወጣው ክፍት የስራ ቦታ 10 የኮምፒተር ሳይንስ ተማሪዎች ሲቀጠሩ፣ ከ10ሩ ውስጥ 8 ቱ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ የተመረቁ የትግራይ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን፣ ከእነሱ መካከል ደግሞ ምህረተአብ የአጠቃላይ የድርጅቱ የኢንፎርሜሽን ዋና ሀላፊ ሆኖ መሾሙን ሰራተኖች ይገልጻሉ።
የትግራይ ተማሪዎች እንደማንኛውም ሰው በችሎታቸው ተወዳድረው ቢገቡ ክፋት አልነበረውም የሚሉት ሰራተኞች፣ የቅጥርም ሆነ የሹመት አሰጣጡ በዘረኝነት ላይ ተመስርቶ መሰጠቱ ለአገሪቱም ለተቀጣሪዎቹም መልካም አይደለም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።
ሰራተኞች በተለያዩ የአየር መንገዱ ክፍሎች የሚገኙ የሃላፊነት ቦታዎችም በተመሳሳይ መንገድ በአንድ ብሄር ሰዎች እየተያዙ መመጣታቸውን ይናገራሉ።
አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚሉት ከመከላከያ፣ ከደህንነትና ከፖሊስ በመቀጠል አየር መንገዱ የህወሃት አባላት በብዛት የሚሰባሰቡበት ቦታ ሆኗል። መንግስት ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሲነሳበት የቆየውን ክስ ፣ ከልምድ ጋር በማያያዝ ለመከለከል ሙከራ ሲያደርግ ቢቆይም፣ ከአየር መንግድ ጋር በተያያዘ ለሚቀርብበት የዘረኝነት ክስ ምላሽ አልሰጠም። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በመንግስት ወጪ ወደ ውጭ አገር ለትምህርት ከሚላኩት መካካል ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የዚህ ብሄር ተወላጆች ናቸው።
በአየር መንገዱ ውስጥ ስለሚታየው ዘረኝነት የድርጅቱን ሃላፊዎች ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

Source:: Ethsat

ቤት ሰሪ የመንግሰት ሰራተኞች አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ


መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ የ1997ቱን ምርጫ ውጤት ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ የነበረው ኢህአዴግ የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የቤት ፈላጊዎችን በማህበር ካደራጀ በሗላ ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ እንዲቆጥቡ በማድረግ ከ9 ዓመታት በሗላ የቤት መስሪያ ቦታቸውን ለቤት ሰሪዎች ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጅ ቤቱን መስራት የሚችሉት መንግስት ባወጣላቸው የቤት እቅድ መሰረት ባለፎቅ ቤት ብቻ መሆኑ ቤት ሰሪዎችን ድንጋጤ ላይ ጥሎአቸዋል። የቤቱን መሰረቱን ካላወጣችሁ የቆጠባችሁት 80ሺ ብር አይመለስላችሁም በመባላቸው ፣ እነዚህ ከ90 በመቶ በላይ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት የቤት ፈላጊዎች የቤቱን መሰረት ለማውጣት የሚያስችል ገንዘብ እንደሌላቸውና የሚኖሩበት የኪራይ ቤት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋው እየጨመረ መምጣቱን በመግለፅ ለዘጠኝ ዓመታት የቆጠቡት ገንዘብ እንዲመለስላቸው በምሬት ቢጠይቁም ምላሽ አላገኙም፡፡
አንዳንድ በጣት የሚቆጠሩ የማህበር አባላት ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ስላላቸው መሰረቱን ማውጣት የቻሉ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ ቦታውን ለመሸጥና ሌላ አማራጭ ለመፈለግ ሁኔታው እያስገደዳቸው ነው፡፡ በዚህ አዲስ የመኖሪያ መንደር መንገድ ፣ ውሃና መብራት መንግስት ሊያስገባላቸው እንዳልቻለ ግንባታውን የጀመሩ አባላት ይናገራሉ፡፡
ከፍተኛው የመንግስት ደሞዝ ጣሪያ ከ5000 ብር በማይበልጥበትና የኑሮ ውድነቱ እጅግ በናረበት ሁኔታ ቤተሰብ መስርቶ በኪራይ ቤት ለሚኖር ሰው መንግስት በሰጠው የቤት ፕላን መሰረት ብቻ ቤት እንዲሰሩ መደረጉ ከስህተትም የከፋ ነው ሲሉ ሰራተኞች ይገልጻሉ። በሌላ ዜና ደግሞ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቦሎቄ እንዲያመርቱ ምክርና ድጋፍ የተደረገላቸው አርሶ አደሮች ምርቱን የሚሸጡበት
የገበያ ሁኔታ እንዳልተመቻቸላቸውና ምርቱ ሲደርስ መንግስት ችላ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ የገበያው ሁኔታ ያስጨነቃቸው በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የሌሎች የምግብ ሰብሎች ዋጋ ይጨምራል ብለው በመስጋታቸው ነው፡፡ እነዚህ አርሶ አደሮች ፣ ” የ ቦሎቄ ዋጋ መውረዱን ተከትሎ የሌሎች መሰረታዊ የምግብ
ፍጆታና ቁሳቁሶች ወጪ በሚሸፍን ዋጋ መሸጥ ካልቻሉ ” አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ይናገራሉ። መንግስት ለውጭ ገበያ በማሰብ ብቻ አርሶ አደሮች ቦሎቄ እንዲያመርቱ ካደረገ በሗላ፣ ሌሎች የገበያ አማራጮችን ባለማመቻቸቱ በውጭ የገበያ ዋጋ ብቻ ተወስነው እንዲሸጡ እየተገደዱ መሆኑን አክለው ይገልጻሉ።

Source:: Ethsat

ብሪታኒያ በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ልትልክ ነው።


መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን እንዳስታወቁት ወታደሮቺ የሚላኩት አልሸባብን እየተዋጉ ላሉት የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ድጋፍ ለመስጠት ነው።
በመሆኑም እስከ 70 የሚደርሱ የ እንግሊዝ ወታደሮች በቅርቡ የሰላም አስከባሪ ልኡኩን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ብሪታኒያ ከዚህም በተጨማሪ እስከ 300 የሚደርሱ ወታደሮቿን በደቡብ ሱዳን እንደምታሰፍር የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
ውሳኔውን አስመልክቶ በመንግስታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ ድጋፍ እንደሚቸራቸው የተገመቱት ዴቪድ ካሜሩን ወታደሮቹ ወደ ስፍራው መንቀሳቀሳቸው ወደ አውሮፓ የሚደረግን ህገወጥ የስደተኞች ዝውውር ለመግታት እንደሚረዳም ተናግረዋል።
በስብሰባው ከዴቪድ ካሜሩን ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራሉ ተብለው ከሚጠበቁት በርካታ የ ዓለማችን መሪዎች መካከል የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኪ መሀመድ አንዱ መሆናቸውም ተመልክቷል። አልሸባብ መላው ሶማሊያን ለመቆጣጠር ከሶማሊያ ጊዜያዊ መንግስት ጋር እየተዋጋ ያለ ጽንፈኛ ድርጅት መኾኑ ይታወቃል።
በቅርቡ ወደ ሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የብሪታንያ ጦር የስልጠና፣ የህክምና፣ የስንቅና የኢንጂነሪንግ ድጋፍ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
ወደ ደቡብ ሱዳን የሚነሳቀሰውም እንዲሁ የስልጠና እና የኢንጂነሪንግ ድጋፍ በመስጠት አስፈላጊ መሰረተ-ልማቶች በሚጠናከሩበት ሁኔታ ድጋፍ እንደሚሰጥ የዜና አውታሩ ጠቁሟል።
በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ታማኞች እና በቀድሞ ምክትላቸው በሪክ ማቻር ደጋፊዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ እስካሁን 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ደቡብ ሱዳናውያን መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንደተሰደዱ ይነገራል።

Source:: Ethsat

Sunday, September 27, 2015

‘የተንዳሆ ግድብ ለዓመታት ተጓተተ” የሚለው የኢቢሲ ዘገባ... “ለዓመታት የተጓተተ ዘገባ” ነው!


Written by  ዮሃንስ ሰ

• ኢቢሲ፣ ይሄን ዘገባ ሰሞኑን ያሰራጨው የት ከርሞ ነው?

1. ወጪው ከ1 ቢ. ብር በታች ነው የተባለው ግንባታ፣ ከ5 ቢ. ብር በላይ ፈጅቶም አላለቀም። 
2. ቢበዛ በ3 ዓመት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል የተባለው ግድብ፣ 10 ዓመት አልበቃውም።
3. ግድቡ እየተጓተተ ወጪው እንደናረ፣ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አድማስ ሲዘገብ ቆይቷል።
4. በ2006 ዓ.ም፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ ግንባታው መዝረክረኩን ገልጿል - (አዲስ አድማስ)።
5. ነገሩ ሲባባስም፣ አምና፣ የገንዘብ ሚ.ር፣ ለግድብ በጀት አልመድብም ብሏል። (አዲስ አድማስ)።
6. የመንግስት ሚዲያ (ኢቢሲ) እና የመሳሰሉ፣ እነዚህን ዘገባዎች፣ “ጨለምተኛ” ሲሏቸው ነበር።

    ከአንድ ቢሊዮን ብር በታች ይፈጃል ተብሎ በ1997 ዓ.ም የተጀመረው የተንዳሆ ግድብ ፕሮጀክት፣ በሁለት ወይም በሦስት ዓመት እንዲጠናቀቅ ነበር የታሰበው። ምን ዋጋ አለው? ወጪው ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል። አስር አመትም ሞላው። ግን ግንባታው አላለቀም። የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ ትልቅ ኪሳራ ነው።
በዚህ መሃል…ኢቢሲ፣ ድንገት ተነስቶ፣ ይህንን የኪሳራ መረጃ ዘንድሮ የሚነግረን፣ የት ከርሞ ነው? ላለፉት ስድስት አመታት የት ነበር? “የግድቡ ግንባታ፣ በተያዘለት እቅድ፣ እየተከናወነ ነው” የሚል... ከእውነት የራቀ፣ ‘የሌለ’ ዜና ለመስራት ሲተጋ ነበር፡፡ ለዚያውም ለበርካታ አመታት።
እና፣ አሁን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረና ነው፣ ‘ግንባታው ተጓተተ፤ ወጪው ሸመጠጠ’ የሚል ዜና የሚያቀርብልን? ምናልባት፣ በአዲስ መንፈስ፣ ‘ከእንግዲህ ትክክለኛ ዜና እሰራለሁ’ የሚል፣ የአዲስ አመት እቅድ አውጥቶ ይሆን? ቢሆንማ፣ ጥሩ ነበር።
ግን አይደለም። “ትክክለኛ ዜና የመስራት እቅዱ፣ ለተንዳሆ ግድብ ብቻ ነው” ካልተባለ በቀር ማለቴ ነው። እንዴት ካላችሁ፣... ኢቢሲ፣ ከተንዳሆ ዜና ጎን ለጎን፣ ስለ ህዳሴ ግድብ ያቀረበውን ዜና መመልከት ትችላላችሁ።  
ኢቢሲን ስትከፍቱ፣ “የሕዳሴ ግድብ ግንባታ፣ በተያዘለት እቅድ በጊዜው እየተከናወነ ነው” የሚል ዜና መስማታችሁ አይቀርም። ለሕዳሴ ግድብ፣ ከፍተኛ ክብር ያላቸው ብዙ ኢትዮጵያዊያን፣ ዜናውን በትኩረት አዳምጠውት ይሆናል። በእርግጥ፣ በየጊዜው የሚደጋገም ዜና ስለሆነ፣ ‘ሳልሰማው አመለጠኝ’ የምንለው አይነት ዜና አይደለም። ባለፈው ሳምንት ቢያመልጣችሁ፣ ከዚያ በፊት በወዲያኛው ሳምንት፣ ተመሳሳይ ዜና ሰምታችሁ ሊሆን ይችላል። ካልሆነም፣ በያዝነው ሳምንት ትሰሙታላችሁ፤... ወይም በሚቀጥለው ሳምንት።
የሕዳሴ ግድብን የሚመለከት፣ የግንባታ ዜና እየተደጋገመ መምጣቱ አይደለም ችግሩ። የሕዳሴ ግድብ፣ እንደ ትልቅነቱ፣ በየጊዜው ከግንባታው ሂደት ጋር ብዙ አዳዲስ መረጃዎች ይኖራሉ። በዚህም ምክንያት፣ የሕዳሴ ግድብ፣ በተደጋጋሚ የዜና ርዕስ ሲሆን ብንሰማ፣ ችግር የለውም። ችግሩ ሌላ ነው። የተሳሳተ መረጃና የውሸት ዜና፣ (ለዚያውም እየተደጋገመ) መምጣቱ ነው ችግሩ።
ኢቢሲ፣ እንደተለመደው፣ “የሕዳሴ ግድብ ግንባታ፣ በተያዘለት እቅድ፣ በጊዜው እየተከናወነ ነው” ካለ በኋላ፤ የግድቡ ግንባታ፣ 47% ላይ መድረሱን ገልጿል። ከምር ለመናገር፣ በትልቅነቱ የሚጠቀስ ግድብ፣ የዚህን ያህል ተገንብቶ ማየት፣ ቀላል ነገር አይደለም። ብዙ ተሰርቷል። ኢቢሲ፣ ይህችን እውነተኛ ዜና ብቻ መግለፅ እየቻለ፣ “በተያዘለት እቅድ፣ በጊዜ እየተከናወነ ነው” የሚል ውሸት ለምን ይጨምርበታል? ግራ ያጋባል።
‘ከተያዘለት እቅድ ዘግይቷል።  ግንባታው ግን 47% ደርሷል’ ብሎ እንዲዘግብ መጠበቅ ያስቸግራል። ቢያደርገውማ፣ “the truth, the whole truth, nothing but the truth” እንደሚባለው፣ እውነተኛ መረጃ... የተሟላ እውነተኛ መረጃ፣... ሌላ ነገር (ውሸት) ያልተቀላቀለበት እውነተኛ መረጃ… ይሆን ነበር።
ግን፣ እሺ... ይቅር። እውነተኛ መረጃን አሟልቶ ለመናገር ፈቃደኛ አይሁን። ግንባታው መዘግየቱን ሳይገልፅ ይተወው። ጎደሎ መረጃ መናገር ይችል ነበር - ግንባታው፣ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ብቻ መግለፅ! ያው፣ ‘የተሟላ እውነት’ አይደለም። ግን፣ ቢያንስ ቢያንስ... ውሸት አልተቀላቀለበትም። አይደለም?
ለነገሩ ይህንን እንተወው። ኢቢሲ፣ ‘እንዲህ ቢያደርግ’፣ ‘እንዲያ ቢያደርግ’ እያልን ለምን በከንቱ እንደክማለን። ኢቢሲ፣ ለዚህ ሁሉ ደንታ ያለው አይመስልም። ደንታ ቢኖረው ኖሮ፣ በየጊዜው እየደጋገመ በድፍረት፣ የሃሰት መረጃ ይናገር ነበር? አገር ምድሩ የሚያውቀው የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ፣ የሃሰት መረጃ መናገር... ሌላ ምን ትርጉም ይኖረዋል? በጣም ቀላል ጉዳይ ነዋ።      
የግድቡ ግንባታ፣ “በአምስት አመት ውስጥ ይጠናቀቃል” ተብሎ እንደነበር ማስታወስ ያቅተናል? አሁን፣ አራት አመት ተኩል ሆኖታል። ግንባታው ግን፣ ወደ ማጠናቀቂያው ሳይሆን፣ ወደ ግማሽ ነው እየተጠጋ ያለው። ቢያንስ፣ ተጨማሪ አራት አመታት ያስፈልጉታል ማለት ነው። ኢቢሲ፣ ይህንን ሳይገነዘብ ቀርቶ ይሆን፣ ቀን ከሌት የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጨው? እንዴት ሊሆን ይችላል?
አሁን አይደለም፣... ከአመት ከሁለት አመት በፊትም፣ የግንባታ ሂደቱንና አዝማሚያውን ለመገንዘብ ከባድ አልነበረም። ከሦስት ዓመት በፊት፣ መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም፣ በአዲስ አድማስ የወጣውን ዘገባ ማየት ይቻላል።
የመንግስት ፕሮጀክቶችን በሚዳስሰው በዚሁ ዘገባ ላይ፣ የሕዳሴ ግድብ ተጠቅሷል። የሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት፣ የታቀደለትን ያህል እየፈጠነ እንዳልሆነ ዘገባው ገልፆ፤ በዚያ አያያዙ፣ ግንባታው ከስምንት እስከ አስር አመት ሊፈጅ እንደሚችል ይጠቁማል። ይሄ ከሦስት ዓመት በፊት የወጣ ዘገባ ነው። በእርግጥም፣ አሁን እንደሚታየው፣ ግድቡ በተያዘለት ጊዜ (ማለትም ዘንድሮ) ሊያልቅ አይችልም። ግማሽ ያህል ይቀራል።
ይሄ፣ መንግስትን የመተቸት ወይም የማወደስ፣ የመደገፍ ወይም የመቃወም ጉዳይ አይደለም። ጥሬ መረጃ ነው። ችግሩ፣ ኢቢሲ፣ ለእንዲህ አይነት መረጃ፣ “ፊት የሚሰጥ” አልሆነም። ግን፣ አስቡት። ችግሮችን በመደበቅ፣ ማስተካከል አይቻልም። “ችግር አለ” ብለን ካልተናገርን፣ “ችግር ብን ብሎ የሚጠፋ” ይመስል! “በተያዘላቸው እቅድ እየተከናወኑ ነው” ብሎ መናገር ብቻውን፤ “የእቅድ ክንውን” ሆኖ ይመዘገባል ካልተባለ በቀር።
ለእውነተኛ መረጃ፣ “ፊት የማንሰጥ” ከሆነ፣ የመጓተትና የመዘግየት ችግሮች ሲያጋጥሙ፣ ተገቢውን ያህል ትኩረት የሚያገኙበትም ሆነ የሚስተካከሉበት እድል እንዴት ይፈጠራል?
በተንዳሆ እና በሌሎች የስኳር ፕሮጀክት ላይ ያየነው ኪሳራ፣ ሳይስተካከልና መፍትሄ ሳያገኝ ለአመታት እየተባባሰ የመጣውም በዚሁ ምክንያት ነው። ስለ ተንዳሆ ግድብም ሆነ ስለሌሎቹ ፕሮጀክቶች፣ ኢቢሲ መረጃ ሳያገኝ ወይም ችግሩን ሳይገነዘብ ቀርቶ ነው?
እሺ፣ አላወቀም፤ አልተገነዘበም እንበል። ግን፣ ለማወቅና ለመገንዘብ ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ፣ ቀላል ዘዴዎችን አያጣም ነበር። በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የወጡ ዘገባዎችን ማንበብ፣ ያን ያህል ከባድ ስራ አይደለም።
ሌሎች የስኳር ፕሮጀክቶች፣ የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክትም ጭምር፣ በ1997 ዓ.ም በወጣላቸው እቅድ እየሄዱ እንዳልሆነ፣ በ2001 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ሲዘገብ አስታውሳለሁ።
የተንዳሆ ግድብ፣ በ98 ዓ.ም፣ ከዚያም በ99 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር በጀት ተመድቦለት በፓርላማ ከፀደቀ በኋላ፣ ምን እንደተከሰተ የሚዘረዝር ሌላ ሰፊ ዘገባም በዚሁ ጋዜጣ ቀርቧል። በሰፊው መቅረቡ አለምክንያት አይደለም። በየአመቱ የሚመደበው ገንዘብ ቀላል አይደለም። ከመቶ ሚሊዮን ብሮች እስከ ቢሊዮን ብር ይደርሳል። ግን፣ ግድቡ ተገንብቶ አላለቀም። እንደገና፣ የ2000 ዓም. በጀት ሲዘጋጅም፣ ገንዘብ ተመደበለት - የግድብ ግንባታውን ዘንድሮ ለማጠናቀቅ በሚል። ግን አልተጠናቀቀም።
በቀጣዮቹ አመታትም... በ2003፣ ከዚያም በ2004... ምንም የተቀየረ ነገር የለም። የበጀት ሰነዶቹ ላይ፣ አረፍተ ነገሮቹ እንኳ አይቀየሩም። “የተንዳሆ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቀ...” የሚለው ፅሁፍ “ኮፒ ፔስት” እየተደረገ በየአመቱ ይደጋገማል - ዓመተ ምህረቱ ብቻ እየተቀየረ።
የመንግስት ቴሌቪዢን ግን፣ እውነታውን ከመዘገብ ይልቅ (እናም መፍትሄ እንዲበጅለት ከማሳሰብ ይልቅ)፣ የአዲስ አድማስ አይነት ዘገባዎችን ለማስተባበል ነበር የሚተጋው - ፕሮጀክቶቹ፣ በተያዘላቸው እቅድ በጊዜ እየተገነቡ ነው’ እያለ።
ለዚህ ምላሽ እንዲሆንም ይመስላል፣ “እንደ ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመሳሰሉ ትልልቆቹ እቅዶች’ኮ ለአመታት እየተጓተቱ እስከ ዛሬ መዝለቃቸውን ራሱ መንግስት አይክደውም” የሚል ፅሁፍ በአዲስ አድማስ የታተመው (ሰኔ 2 ቀን 2004 ዓ.ም)። “መቼ ነው መንግስት፣ የማይሳኩትን እቅዶች በግልፅ የሚነግረን” በሚል ርዕስ የቀረበ ትንታኔ ላይ ከተጠቀሱት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ፣ የተንዳሆው ፕሮጀክት ነው። አዲስ አድማስ እንዲህ፣ እውነተኛ መረጃዎችን በመስከረም 2005 ዓ.ም ሲዘግብ፣ የመንግስት ሚዲያ በዚያ ሰሞን ምን ዘገበ?
መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም የኢዜአ ርዕስ እንዲህ ይላል - “የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በቀጣዩ ጥር ወር በከፊል ወደ ሥራ ይገባል”።
ለነገሩ፣ የመንግስት ሚዲያ፣ በቀላሉ ለእውነተኛ መረጃ “ፊት ይሰጣሉ” ብሎ መጠበቅ አስቸጋሪ እንደሆነ ለመረዳት ከፈለጋችሁ፣ የፌደራል ዋና ኦዲተርን ሪፖርት መመልከት ትችላላችሁ። የተንዳሆ ፕሮጀክት፣ እጅጉን እንደተጓተተና በከፍተኛ የሃብት ብክነት እንደተዝረከረከ፣ ዋናው ኦዲተር ሰፊ ዝርዝር ሪፖርት ያቀረበው በ2006 ዓ.ም ነው። አዲስ አድማስ ይህንን ዘግቧል። በመንግስት ሚዲያ ግን አልተዘገበም።
ሰሞኑን ድንገት ተነስቶ ግን ፕሮጀክቱ ለዓመታት መጓተቱን የሚገልጽ ዘገባ አሰራጨ፡፡ ለዓመታት ለተጓተተ ፕሮጀክት ለዓመታት የተጓተተ ዘገባ !!

Source:http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=16915%3A%E2%80%98%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%88%86-%E1%8C%8D%E1%8B%B5%E1%89%A5-%E1%88%88%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B3%E1%89%B5-%E1%89%B0%E1%8C%93%E1%89%B0%E1%89%B0%E2%80%9D-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%88%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%A2%E1%88%B2-%E1%8B%98%E1%8C%88%E1%89%A3-%E2%80%9C%E1%88%88%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B3%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8C%93%E1%89%B0%E1%89%B0-%E1%8B%98%E1%8C%88%E1%89%A3%E2%80%9D-%E1%8A%90%E1%8B%8D

ይቅርታ- የወያኔ ካርታ (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

1437ኛው የኢድ አል አድኻ ( አረፋ) በአል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲከበር ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ አስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በሽብር ወንጀል ተከሰው ከተፈረደባቸው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል ስድስቱ በቅርቡ የተለቀቁት በእነርሱ ጥያቄና ጥረት አንደሆነ፤ ጥያቄአቸው ምላሽ በማግኘቱና ጥረታቸው በመሳካቱ መደሰታቸውን ገልጸው ለመንግሥት ምሥጋና ማቅረባቸውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላላፈው ዘገባ አሰምጾናል፡፡ ወያኔ ግዜና ወቅት እየጠበቀ የሚጠቀምባት የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ የይቅርታ ካርድ በሌላ መንገድና መልክ ተመዘዘች ማለት ነው፡፡

ይቅርታ መጠየቃቸው ተሰምቶ ሳይፈቱ አመታት ያስቆጠሩ፤ በአንጻሩ ይቅርታ መጠየቅ ቀርቶ በፍርድ ቤቱ አምነት የለንም በማለት የፍርድ ማቅለያ እስተያየየት አናቀርብም ያሉ ይቅርታ ጠየቁ ተብሎ ሲፈቱ፤ እንዲሁም ወራት በፈጀ የሽምግልና ጥረት የተፈቱ ፖለቲከኞች ወያኔ የጭንቁን ግዜ ሲያልፍ ክዶ ሽምግልና ብሎ ነገር የለም በህግና በህግ ብቻ ነው የተፈቱት ወዘተ እያለ በይቅርታ ፖለቲካ ሲቆመር አይተናል ሰምተናል፡፡

ወያኔዎች ይህን የሚፈጽሙት የይቅርታ ሥነ ሥርዐት አዋጁ ከጠረጰዛቸው ላይ ተቀምጦ ጻፋችሁኝ እንጂ አታውቁኝም፣ አወጃችሁኝ እንጂ አትተገብሩኝም እያለ እንዳያፌዝባቸው፣ ሌላውም ሰው አውቆትና ተረድቶ እንዳይጠይቅ መሳቢያ ውስጥ ቆልፈው ነው፡፡ በመሆኑም በየደረጃው በትንሽም በትልቅም ሀላፊነት ላይ ያሉ የሚሰሩት ህጉን አውቀው ሳይሆን በአለቆቻቸው የሚታዘዙትን ነው፡፡ ከተቀዋሚውም በአብዛኛው የሚሰማው ጩሁትም ሆነ ተቃውሞ ወያኔ ከሚሰራውና ከሚናገረው በመነሳት እንጂ አዋጁን መሰረት ባደረገ አይደለም፡፡

ይቅርታ ምንድን ነው? ማነው የሚጠይቀው የሚጠየቀውስ? መቼና እንዴትስ ነው የሚጠየቀውˆ የሚሉትን ጥያቄዎች ምላሽ ማወቅ ወያኔ ይቅርታን የፖለቲካ መቆመሪያ ካርታ አድርጎ እየሰራበት መሆኑን በበቂ ማረጋገጥ ያስችላል፡፡ እናም ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ የአዋጅ ቁጥር 395/1996 አንቀጾችን ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡

የይቅርታ ጥያቄ ማለት? ይህ ዐዋጅ ትርጓሜ በሚለው ክፍሉ አንቀጽ 4 “የይቅርታ ጥያቄ ማለት አንድ ፍርድ በሙሉ ወይንም በከፊል ቀሪ እንዲሆን ወይም የቅጣቱ አፈፃፀምና ዓይነት በቀላል ሁኔታ እንዲፈፀም የሚቀርብ ነው” በማለት ይተረጉማል። በአንቀጽ 2(3) ደግሞ “ፍርድ ማለት በወንጀል ጉዳይ በፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ የተወሰነ ዋና ቅጣት፣ ተጨማሪ ቅጣት ወይንም የጥንቃቄና ጥበቃ ውሳኔ ነው” ይላል።

የይቅርታ ጥያቄ የሚቀርበው በማን ነው? ስለ ይቅርታ ጥያቄ አቀራረብ የሚገልፀው የዐዋጁ ክፍል፤ስድስት ንዑሳን አንቀጾች ያሉት ሲሆን ንዑስ አንቀጽ 1 “በወንጀል ጉዳይ በፍ/ቤት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ የተፈረደበት ማንኛውም ሰው፣የተወሰነው ፍርድ በሕግ ይቅርታ የሚያስከለክል ካልሆነ በስተቀር የይቅርታ ጥያቄውን ራሱ ወይንም በባለቤቱ፣ በቅርብ ዘመዶቹ፣ በወኪሉ ወይም በጠበቃው አማካኝነት ማቅረብ ይችላል”ይላል፡፡

ይህ አንቀጽ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮችን መያዙን ልብ ማለት ያሻል። ይሄውም አንደኛ የይቅርታ ጥያቄው መቅረብ የሚችለው ከመጨረሻ ፍርድ በኋላ መሆኑንና ሁለተኛ ጥያቄው በማን እንደሚቀርብ በግልፅ የሚያሳይ መሆኑን።

የዐዋጅ አንቀጽ 12(2) ደግሞ የፍትህ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን፣ ይቅርታ ሊደረግላቸው የሚገባቸውን ሰዎች በመምረጥ የይቅርታ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ ይገልፃል።

ይቅርታ የሚጠየቀው መቼ ነው? የይቅርታ ጥያቄ መቼ እንደሚቀርብ ግልፅ የሚያደርገውና ይህንኑ ብቻ የሚገልፀው አንቀጽ 14 (1) ፍርዱ ከተሰጠ በኋላ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል በማለት በማያሻማ ሁኔታ በግልፅ አስፍሯል።

የይቅርታ ጥያቄ የሚቀርበው ለማን ነው? የይቅርታ ጥያቄ የሚቀርበው የይቅርታ ቦርድ (ኮሚሽን) ተብሎ ለተሰየመው ተቋም ሲሆን የሱ ተግባርም በአዋጁ አንቀጽ 4(1) የይቅርታ ጥያቄውን በመመርመር የውሳኔ ሀሳብ ለፕሬዝዳንቱ ማቅረብ እንደሆነ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

ይቅርታ የሚሰጠው ማነው? ይቅርታ መስጠትም ሆነ መንሳት ብሎም የተሰጠን ይቅርታ ማንሳት በአዋጅ ሳይሆን በህገ መንግሥቱ ሥልጣን የተሰጠው ለፕሬዝዳንቱ ነው፡፡ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሚባለው (የሚባለው ያልኩት በተግባር የሕጎች ሁሉ የበላይ መሆን ቀርቶ የባለሥልጣናትም የበላይ ለመሆን ባለመቻሉ ነው) ሕገ መንግስት የፕሬዝዳንቱን ተግባርና ኃላፊነት በዘረዘረበት በአንቀጽ 71 በንዑስ አንጽ 7 ላይ “በህግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል” በማለት ሥልጣን የሰጠው ለፕሬዝዳንቱ ብቻ ነው፡፡

አዋጁ ይቅርታ መስጠት መከልከልና የተሰጠን ይቅርታ ማንሳትን በተመለከተ በግልጽ የደነገገ ቢሆንም ህግን ሊገዛበት ሳይሆን ሊያስመስልበት የሚያወጣው፣ ወያኔ ይቅርታን የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ካርድ አድርጎ ሲጠቀምበት ይህ አዋጅ ከነመኖሩም የሚያስታውሰ አይመስለኝም፡፡

በርግጥ ህገ መንግሥትን ያህል ነገር እንዳሻው የሚደፈጥጥ ቡድን አዋጅ ቢሽር& ደንብ ቢተላለፍ፤በፍትህ ቢያላጋጥ ብዙ ሊገርም አይችልም፡፡ ዳኞች በስልክ ትዕዛዝ በሚፈርዱበት፣አቃቤ ህጎች አቃቤ ወያኔ ሆነው በሀሰት በሚከሱበትና አባይ ምስክር እያሰለጡኑ በችሎት በሚጋለጡበት፤ ዜጎች ያለምክንያት ታስረው ያለምክንያት በሚፈቱበት፤ ፖሊስ፤ዳኛ፤ የወህኒ ቤት ኃላፊዎች፤ደህንነት፤ማን የበላይ አንደሆነ በማይታወቅበት፤ፍትህ ሳይገነዝ በተቀበረበት ሥርአት ውስጥ የሚነገር የሚፈጸመው ሁሉ አዲስ እየሆነ ሊደንቀን አይገባም፡፡ ምክንያቱም ወያኔን በሚገባ አውቀነዋልና፡፡ ከዚህ ውጪ መልካም ነገር ከሱ መጠበቅ ካቆምን ቆይተናልና፡፡ ይልቁንስ በህግ አምላክ ሲባል እንኳን ሰው የወንዝ ውኃ ይቆማል ይባልላት የነበረችን ሀገር ጨርሶ ህግ አልባ ከማድረጉ በፊት መገላገያውን መላ መምታት ነው የሚሻለው፡፡

በኢትዮጵያ የፍትህ አስተዳደር የሚታዩ ችግሮችና የፖሊስ ነጥቦች የውይይት መነሻ ሀሳቦች በጥላሁን ተሾመ ተባባሪ ፕሮፌሰርና ዲን ሕግ ፋክልቲ አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በሚል በቀረበ 11 ገጽ ጽሁፍ (ቀንና አመተ ምህረት የለውም ) ወያኔ ምክር አያሰማም አንጂ የጽሁፉ አቅራቢ በማጠቃላያቸው ላይ አንዲህ የሚል ምክር አቅርበው ነበር፡፡

{የፕሮፓጋንዳ ፍላጎታችንን ለማርካት ብለን ሳይሆን፣የግል ወይንም የቡድን ዓላማዎቻችንን ለማራመድ ብለን ሳይሆን፣ ከሌሎች የህግ ሥርዓቶች ለመፎካከርና እንዲህ ነን ለማለትም ሳይሆን ፣ታግለንለታል እየታገልንለትም ነው ለምንለው ሕዝባችን መብትና ነጻነት ብለን የፍትህ ሥርዓታችንን እንደገና የምንፈትሽበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ጀንበሯ ልትጠልቅብን ሩብ ሰዓት ብቻ ቀርቷታልና፡፡}

ስለ ይቅርታ ከተነሳ አይቀር ወያኔዎች ጠዋት ማታ ከሚምሉለትና ከሚገዘቱለት ነገር ግን ከማያውቁትና ከማይገዙበት ሕገ መንግሥት አንድ አንቀጽ ላስታውሳቸው፡፡ የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 28/1 {ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች የሰው ዘር የማጥፋት ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ወይም ኢሰብአዊ የድብደባ ደርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፣ በህግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት ውሳኔዎች በምህረት ወይንም በይቅርታ አይታለፉም፡፡} ይላል፡፡ወያኔዎች ይህን አንቀጽ ሲጽፉ የደርግ ባለሥልጣን በማለት ያሰሩዋቸውን ሰዎች እያሰቡ ይመስላል፡፡እስቲ የራሳቸውን ድርጊት ከዚህ አንቀጽ ጋር ለአፍታ ያገናዝቡት፡፡

ለመሰናበቻ ከላይ ከገለጽኩት ከፕ/ር ጥላሁን ጽሁፍ አንድ አንቀጽ ልጥቀስ፡፡

“ሕዝብ ከመንግሥት የሚጠብቀው ዋንኛ አገልግሎትም ፍትሕ ማስፈንን ነው፡፡ በተረፈ ገበሬው አርሶ፤ነጋዴውም ሸቅሎ፣ ሠራተኛውም ለፍቶ ነው፡ ሕይወቱን የሚመራው፡፡ የተለየ ችግር ካላጋጠም በስተቀር ሕዝብ መንግሥትን አብላኝ አጠጣኝ ወይንም አኑረኝ አይለውም፡፡ ይልቁንም አስተማማኝ የፍትህ ሥርዓት በመኖሩ ሕዝቡ ራሱ መጠቀሙ ብቻ ሳይሆን መንግሥትንም ይጠቅመዋል፡፡ፍትህ ሲኖር ሀገር ይለማል፣ ሀገር ሲለማም መንግሥት ይጠነክራል፡፡ ፍትህ ሲኖር ሰላም ይሰፍናል፣ሰላም ሲሰፍን ሕዝብ በመንግሥት ላይ አመኔታ ይኖረዋል፡፡ ፍትህ ሲኖር ሕዝብ ይሰራል፣ገቢም ያገኛል፡፡ከዚህ ሂደትም መንግሥት በልዩ ልዩ መንገዶች ይጠቀማል፡፡ሕብረተሰቡም ከሕገ-ወጦች ከሁሉም በላይ ደግሞ መረን ከለቀቀና ከጨቋኝ መንግሥታዊ አስተዳደር ይጠበቃሉ፡”

Source : http://ecadforum.com/Amharic/archives/15637/

Friday, September 25, 2015

በኬንያና ማላዊ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ላይ ናቸው Posted by


መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ኢዞሎ ግዛት ውስጥ ድንበር አቋርጠው ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተጨናነቀ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ዘግቧል።
በኬንያ ኢዞሎ ጂኬ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት 450 እስረኞች መካከል 300 ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እስር ቤቱ ከ 150 የበለጡ እስረኞችን መያዝ እንደማይችል የኢዞሎ ግዛት ምክትል ኮሚሽነር ገልጸዋል።
በኬንያ ውስጥ የሚገኙ ሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪዎችን አድኖ ለመያዝ እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ባለስልጣኑ፣ የእስር ጊዜያቸውን የጨረሱ ሰማንያ ኢትዮጵያዊ እስረኞች ባለፈው ወር ወደ አገራቸው መጠረዛቸውንና መቶ ሃያ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በሜሩ ግዛት ውስጥ ፍርድቤት መቅረባቸውን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙት ዜጎቹን ለማስለቀቅም ሆነ ለመጎብኘት ምንም ዓይነት ጥረት እስካሁን ድረስ አላደረገም።
በማላዊ እስር ቤት ውስጥ ደግሞ 387 እስረኞች ሲኖሩ፣ ሰላሳ ስድስቱ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች በዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም አማካኝነት ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።
ከተመለሱት መካከል ሕፃናት እንደሚገኙበትና በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዩጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ አድርገው ሞዛምቢክና ዛምቢያን አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገወጥ መንገድ ይገባሉ።
በተጨማሪም የግብፅን ድንበር ጥሰው የሲና ባሕረ ሰላጤ የዋሻ መሸጋገሪያን በመጠቀም ወደ እስራኤል ሊገቡ ሲሞክሩ የነበሩ 22 ኢትዮጵያዊያንን ተይዘዋል። ከተያዙት መካከል የኤርትራ፣የግብጽ፣የሱዳን፣የኮሞሮስና የሶማሊያ ዜጎች ይገኙበታል።
የአውሮፓ ህበረት ስለሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር እየመከረ ነው።

Source:: Ethsat

በከፍተኛ ወጪ የሚገነባው ፈጣን የአውቶቡስ መስመር ተቃውሞ ገጠመው


መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በየካቲት ወር 2008 ጀምሮ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ
ፕሮጀክት ከአዋጪነት አንጻር በሚገባ በጥናት ያልታየና በአሁኑ ሰዓት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን የሚያሳጣ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ፕሮጀክቱ ከዊንጌት፣ በጎፋ ገብርኤል አድርጎ ወደ ጀሞ የሚዘልቅ ለከተማ አውቶቡስ ብቻ የተከለለ መስመር ለመገንባት የታቀደ ሲሆን ፣ ይህ ፕሮጀክት በጠቅላላው 60 ሚሊየን ዩሮ
ይፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡ ፕሮጀክቱ በየካቲት ወር 2008 ተጀምሮ በ15 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል። ለዚህ ግንባታ የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ 50 ሚሊየን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምቶአል፡፡
ፕሮጀክቱ የሕዝብ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ ያስችላል በሚል የታቀደ ይሁን እንጂ ከአዋጪነት አንጻር ተገቢው ጥናት አልተካሄደበትም ያሉት ምንጮቹ ፣ ይህን መስመር ከመገንባት በርካታ አውቶቡሶችን በማሰማራት የትራንስፖርት ችግርን መቅረፍ ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል ታሳቢ አለመደረጉ አሳሳቢ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ፕሮጀክቱ በዝርዝር የኢንጂነሪንግ ጥናት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአውቶቡስ መስመሩን ለመዘርጋት በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክና የቴሌ መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም በርካታ ሕንጻዎችን የሚያፈራርስ ሲሆን በዚህም ምክንያት በመስመሩ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቀዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ ከህዝብ ጋር ሳይወያይ ወደትግበራ መግባቱ ነዋሪዎቹን ያበሳጨ ሲሆን፣ ብድር ተገኘ ተብሎ ዝም ብሎ ወደቁፋሮ መግባት መንግስታዊ ሌብነትን ከማስፋፋት የዘለለ ትርፍ አያስገኝም ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡

Source:: Ethsat