Wednesday, September 30, 2015

ሰበር ዜና ! ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ታሰረ !

የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት በየመን ወታደሮች ቁጥጥር ስራ መዋሉን ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ችያለሁ ። ጋዜጠኛ ግሩም ላለፉት ሶስት ቀናት ሲታደን መቆየቱን የጠቁሙኝ ምንጮች ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠውልኛል !
የጋዘጠኛ ግሩም መታሰር እንደሰማሁ ወደ የመን ስልክ በመደዎል ያነጋገርኳት ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ በየነንየጋዜጠኛ ግሩምን መታሰር አረጋግጣልኛለች ። ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሃይ ከዚሁ ጋር አያይዛ ጋዜጠኛ ግሩምን ያሳሰረው ኢትዮጵያዊ መሆኑንና የታሰረበትም ምክንያት ” ከተለያዩ ሃገራት በተረጅዎች ስም ገንዘብ ትሰበስባለህ ፣ ወደ ከየመን ውጭ መረጃ ታሰራጫለህ ” የሚል ክስ እንደሆነ ጠቁማኛለች ።
በየመን ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃን ከማቅረብ ባለፈ ፣ ረግተው በማያውቁት የየመን ከተሞችና በርሃ ላይ በአደጋ ተከበው ለሚሰቃዩ ስደተኛ ወገኖች በነፍስ ደራሽ የነበረው ብርቱ ጋዜጠኛ ግሩም የየመኑን የኢትዮጵያን የስደት መከራና ሰቆቃ የሚዳሰወስ “የሞት ጉዞ ” የሚል መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘመጋም !
በጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት እስራት ዙሪያ ስላሉት አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልኩ መረጃ የማቀርብ መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

Source :https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2015/09/30/dew/


No comments:

Post a Comment