Wednesday, October 28, 2015

አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከውጭ ሚ/ር ደኤታነት ተነሱ


(ዘ-ሐበሻ) የሟቹ አምባገን የኢትዮጵያ መሪ የቅርብ ሰው የነበረውና በውጭ ሃገር በተለይም በአሜሪካ እና በብራሰልስ በቆየባቸው ጊዜያቶች የአምባሳደርነት ስም ይዞ የገዢውን ፓርቲ አምባገነን መሪዎችን ገንዘብ በማሸሽ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ቆይቷል እየተባለ በሰፊው የሚተቸው ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ደኤታነት ስልጣኑ ድንገት ተነሳ::

አንዳንድ የቅርብ ምንጮች ብርሃነ ስልጣኑን የለቀቀቀው በፈቃዱ ነው ይበሉ እንጂ ጉዳዩ በአዲስ አበባውና በመቀሌው የሕወሓት ቡድን ክፍፍል ጋር የተያያዘ ነው እየተባለ ነው::

በ2013 ዓ.ም ከደደቢት በረሃ ጀምሮ ለዓመታት ሕወሓት ውስጥ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ያገለገሉት አምባሳደር ስዩም መስፍን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶም ባቀረቡት ጥያቄና ፓርቲው እየተገበረ ባለው የመተካካት ሂደት በሚል ሽፋን መሰረት ሥልጣናቸውን እንዲለቁ የተደረጉ ሲሆን አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ እነዚሁ ባለስልጣናት ወደ ሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለመግባት ጥረት አድርገው ነበር:: በተለይም ከአቶ አርከበ እቁባይ ጋር በጋብቻ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ አቶ አርከበን የሕወሓትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር ለማድረግ ከሚሰራው ቡድን ጀርባ ሆነው ብዙ ሲንቀሳቀሱ ቆይተው በመቀሌው ቡድን በባለፈው የሕወሓት ጉባኤ ላይ መሸነፋቸው ይታወሳል::

አቶ ብርሃነ ከዚህ ቀደም በሕጋዊ ባለቤቱ ላይ ሲወሰልት በመያዙ የቀድሞ ሚስቱ ከዛሬ 12 ና 13 ዓመታት ገደማ በፊት ብርሃነን በዝሙት ጉዳይ ክስ መስርታበት በመረታቱ በርሱ ስም በኒውዮርክ ከተቀመጠው የሕወሃት ባለስልጣናት ገንዘብ ውስጥ ካሳ እንዲሆናት 5 ሚሊዮን ብር እንደተፈረደላት በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ አይዘነጋም::

በአቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ቦታ ሌላ ሚ/ር ደኤታ መሾሙም ተሰምቷል:: ባለስልጣኑ ወደ ሌላ ቦታ ይዘዋወሩ/ አይዘዋወሩ ያገኘነው መረጃ የለም::

The post አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከውጭ ሚ/ር ደኤታነት ተነሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

Source:: Zehabesha

No comments:

Post a Comment