ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን ያጠፋ ሲሆን፣ ባለቤቱም ራሱዋን ስታ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎት እየተደረገላት ነው። ወጣት ታምራት ትናንት ነሃሴ 26 የቀብሩ ስነስርአት ተፈጽሟል። ሚሚ ባቴ የተባለች የአንድ ሳምንት መጫትም በላዩዋ ላይ ቤቷ በመፍረሱ፣ ጎዳና ላይ ወድቃለች። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ወጣቶችም አሉ። እስካሁን ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዚሁ ከተማ ትናንት ምሽት በንግድ ቤቶች ላይ በተነሳ ቃጠሎ ከ100 በላይ የንግድ ድርጅቶች ወድመዋ
No comments:
Post a Comment