Wednesday, September 2, 2015

በደቡብ ኦሞ የሰፈሩ የሰራዊት አባላት መጥፋታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው


ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል።
ከወር በፊት በሃመር ወረዳ በተፈጠረው ግጭት በርካታ የወረዳው ነዋሪዎችና ፖሊስ አባላት ተገድለዋል። ግጭቱን ለማብረድ አንድ ሻለቃ ጦር በተለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍር ተደርጓል። ይሁን እንጅ በወታደሮቹ መካካል መተማመን በመጥፋቱ ከመካከላቸው በርካታ ወታደሮች በመኮብለላቸውና የደረሱበት ባለመታወቁ፣ አመራሮቹ ወታደሮች እንዲጠፉ አድርገዋል ያሉዋቸውን የሞተር አሽከርካሪዎች ይዘው አስረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት አሽከርካሪዎች መካከል ጌታ ጫን ያለው ወርቁ፣ አሚኑ ትኩና አሚኑ ሃሰን ይገኙበታል። አሽከርካሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው፣ ከ15 ቀናት የእስር ጊዜ በሁዋላ በዋስ ሲፈቱ፣ ወታደሮቹን በማሸሹ ሂደት ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ወታደሮች በአርካሻ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ።
በመጀመሪያው ዙር ከጠፉት የሰራዊት አባላት መካከል 7ቱ የከባድ መሳሪያ አስተኳሾች ናቸው።
አንዳንድ የሰራዊቱ አባላት ደግሞ በአካባቢው ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለው ወንጀል በዲመካና ቱርሚ የሚኖሩ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። ወታደሮቹ ህጻናትንና ባለትዳር ሴቶችን ሳይቀር አስገድደው በመድፈር በጤናቸውና በትዳራቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው። የወታደሮቹን ጥቃት በመፍራት የአካባቢው ሴቶች ወደ ጂንካ ከተማ እየኮበለሉ ነው።
እስካሁን ድረስ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል የአቶ አረጋ ባለቤት፣ ለቤተሰባቸውና ለግለሰቦች ደህንነት ሲባል ሙሉ ስማቸውን የማንጠቅሳቸው ባለቤታቸው፣ እና የ11 አመት ህጻን ልጃቸው በወታደሮች ተደፍረዋል። አቶ ቢረጋ በባለቤታቸውና በልጃቸው ላይ ግፉን የፈጸሙትን ወታደሮች ለፍርድ ለማቅረብ ቢንቀሳቀሱም፣ በመርማሪ ፖሊስ ዮሴፍ ክፉኛ ተደብድበው ፣ እንዳይንቀሳቀሱ ተደርጓል።
እንዲሁም የአቶ ገልለሎ ልጅ የሆነችው የ8 አመቷ ህጻን ልጅ፣ በወታደር ከተደፈረች በሁዋላ ራሱዋን ስታ ፣ በዲመካ ጤና ጣቢያ ህክምና ተደርጎላት ከሞት ተርፋለች።
ከደቡብ ኦሞ ዞን ዜና ሳንወጣ ፣ በቅርቡ በዞኑ በደረሰው የመብራት ትራንስፎርመር ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተለይተው ታውቀዋል።
በበና ጸማይ ወረዳ በቃቆ ቀበሌ ነሃሴ 21 ፣ 2007 ዓም በደረሰው ፍንዳታ ፣ በቆቃ ጤና ጣቢያ ላብራቶሪ ሙያተኛ የነበረች ወ/ት ምሳ ታሪኩ አያሌው ወዲያውኑ ህይወቷ ሲያልፍ፣ ወ/ሮ መሰለች ቶጣሮ፣ ወ/ሮ ህይወት አበጀ፣ ወ/ሮ አዲስ አለም ውሉቃ፣ መ/ርት ጥሩየ አድማሴ፣ ወጣት ዘካሪያስ ዮሴፍ፣ አቶ በየነ ክብሪትና አቶ ደጀኔ ተፈሪ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው አሁንም በህክምና ላይ ሲገኙ፣ ሌሎች 13 ሰዎች ደግሞ ታክመው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።
በእለቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ በቃቆ 1፤በቀያፈር 3፤በዲመካ 1፤በጂንካ 2፤በሜጸር 1፤በድምሩ 8 ትራንስፎርመሮች የፈነዱ ሲሆን፣ በቃቆዉ ፍንዳታ የዋናዉ መስመር ሽቦ በመበጠሱ በአካባቢዉ በሚገኘዉ ምግብ ቤት ላይ ወድቆ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ

No comments:

Post a Comment