Monday, August 17, 2015

በአዋሳ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ተሰማ


ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን በላከው ሪፖርት በከተማ ውስጥ ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ሆነ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ ፣ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል።
በርካታ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ቀኑን ሙሉ በየማደያዎች ተሰልፈው የታዩ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የታየው የዋጋ ጭማሪ ህዝቡን ለምሬት ዳርጎታል። በባህርዳርም እንዲሁ በቅርቡ ተመሳሳይ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment