ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ መቋረጥ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ለውጥ የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለያዩ አጎራባች ወረደዎችና ቀበሌዎች ህዝቡ መኪና መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋትና መኪና እንዳይተላለፍ በማድረግ እንዲሁም በጋራ በመሰባስብና ድምጻቸውን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የነበቱ ሲሆን፣ ዛሬም ዩኒቨርስቲው በሚገነባበት አካባቢ ተቃውሞ እንደነበር፣ ጉጉፍቱ አካበባ ደግሞ መንገዶች ተዘጋግተው መዋላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ ሰፍሯል።በሳምንቱ መጨረሻ 2 ወጣቶች ታስረው የነበረ ቢሆንም፣ ወዲያው መፈታታቸውም ታውቋል። አብዛኛው ነዋሪዎች መሳሪያ የታጠቁ በመሆናቸው ባለስልጣናቱ ተቃውሞ የሚያሰሙትን ለማሰር እንደቸገራቸውነዋሪዎች ያክላሉ።
የአካባቢው ባለስልጣናት በሳምንቱ መጨረሻ ያደረጉት ስብሰባ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉና እየተካሰሱ ሳይስማሙ ተለያይተዋል።
ከምርጫው በፊት ም/ል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አቀስታ ላይ ዩኒቨርስቲ እንደሚሰራ የመሰረት ድንጋይ ቢያስቀምጡም፣ ምርጫው ሲጠናቀቅ፣ ዩኒቨርስቲው ለሌላ ወረዳ መሰጠቱ ይፋ መደረጉ ህዝቡን ለተቃውሞ ዳርጎታል።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment