Saturday, June 13, 2015

ምርጫ በሁዋላ ኢትዮጵያዉያን ሌሎች የትግል አማራጮችን እየፈለጉ እንደሆነ ዘጋርዲያን ዘገበ


ኢሳት ዜና (ሰኔ 4 2007 ዓም)
የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች “ ቅድሚያ ለነጻነት ” ወደሚል ትግል ማዘንበላቸውን የእንግሊዝ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ሐሙስ ለንባብ ባበቃው እትሙ ዘገበ።
ገዢው የኢሃዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በብቸኝነት ለድል መብቃቱም በመንግስት ላይ ጥያቄ ያላቸው አካላት ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ ማስገደዱንም ጋዜጣው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል።
በቅርቡ ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጉዳይ በሀገሪቱ ያለውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አደጋ ውስጥ እንደወደቀ ማሳያ ነው ሲል የገለጸው ዘ-ጋርዲያ ጋዜጣ ለእስር የተዳረጉት ተከሳሾች ፈጽመውታል ስለተባለው ህገ-ወጥ ድርጊት እስካሁን ድረስ በከሳሽ አቃቢ ህግ ማስረጃ ሳይቀርብ መቅረቱን አስታውቋል ።
በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አደጋ ውስጥ በመግባቱም ተቃዋሚ ፓርቲዎች “ ቅድሚያ ለነጻነት ” ወደሚል የትግል አቅጣጫ ማዘንበላቸውን ጋዜጣው አስነብቧል።
በሌላ በኩልም በገዢው የኢሃዴግ መንግስት ላይ የተለያዩ ጥያቄ ያላቸው አካላት የተለያዩ አማራጮችን ለማየት ተገደው እንደሚገኙ ጋዜጣው በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ባቀረበው ሰፊ ሪፖርት ገልጿል።
ሀሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ባሉበት ሀገር አሳታፊ የሆነ የፖለቲካ ምህዳር ይኖራል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው ሲል ለደህንነቱ ሲል ስሙን ያልገለጸው አንድ ኢትዮጵያዊ ለጋዜጣው አስረድቷል።
ወደ ሁለት መቶ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክኒያት የሆነው የ 1997 ቱን ደም አፋሳሽ ምርጫ በዘገባው ያወሳው ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ የሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ዳግም በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆኖ እንደሚገኝ አመልክቷል ።
የተለያዩ አካላት የገዢውን የኢሃዴድ አመራሮች መቀያየር የሚመጣው አንዳች ለውጥ እንደሌለ በመግለጽ ሀገሪቱ የሁሉንም ዜጎች የማያሳትፍ የፖለቲካ አቅጣጫ እንዳለበት በማሰብ ላይ ናቸው ሲል ጋዜጣው አስነብቧል ።
በቅርቡ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ በተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ አድርጓል በሚል የተለያዩ አካላት በምርጫው ውጤት ላይ ስጋት እንዳላቸው በመግለጽ ላይ ናቸው ።
የ442 የምክርቤት ወንበሮች በገዢው የኢሃዴግ ፓርቲ እንደተሸነፉ የገለጸው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀሪዎቹን ወንበሮች ውጤት ይፋ ከማድረግ ተቆጥቦ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment