Thursday, September 17, 2015

በለቡ አንዲት የሃያ ዓመት ወጣት በፌደራል ፖሊስ አባል ተገደለች

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በለቡ መዝናኛ ውስጥ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመዝናናት ላይ የነበረችው ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ”አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድ ነው?” በሚል ተልካሻ ምክንያት መሳሪያ የታጠቀው የፌደራል ፓሊስ አባል ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በወቅቱ እራሱንም ለማጥፋት ጭንቅላቱ አካባቢ ላይ ያቆሰለ ሲሆን፣ ሳይሞት በሕይወት መትረፉንና በሕክምና ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተባባሱ መምጣታቸውንና በተለይ ሴቶች ነፍጥ ባነገቡ ኃላፊነት በማይሰማቸው ታጣቂዎች መገደላቸው እየበረከተና እየተባባሰ መጥቷል። ባህርዳር ውስጥ የተፈጸመው ግድያን ጨምሮ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በተደጋጋሚ ጊዜ የተፈጸመ ድርጊት ከመሆኑም በላይ፣ ዜጎች ከሕግ አስከባሪዎች ከለላና ጥበቃ ከማግኘት ይልቅ ፍርሃትና ሽብር ውስጥ መውደቃቸውን ነዋሪዎች በምሬት ይናገራሉ።
የወጣት ሰሎሜ ጉልላት የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment