Saturday, June 13, 2015

60 የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ለ3 ቀናት ግምገማ አካሄዱ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀናት በደብረ ዘይት ከተማ በተካሄደው ግምገማ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የመገምገሚያ ነጥቦቹ “አመራሮቹ በየምርጫ ምደባቸው የነበራቸው ውጤታማነትና ውስጣዊ ስኬት፤ በተቋማቸው የነበረው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግልና የተመዘገበ ውጤት፣ እንዲሁም ግለሰባዊ ድክመታቸው ” የሚሉ ሲሆኑ፣ በግምገማውም
ባለስልጣኖቹ ከኤ እስከ ዲ ያሉ ውጤቶችን አግኝተዋል።
በህወሃት አባላት የሚመሩ ተቋማት ውጤታማ ሲባሉ ፣ ሌሎቹ ደካሞች ተብለዋል። በአመራር የማይቀጥሉ፣ ከሃላፊነት ዝቅ የሚሉና ለከፍተኛ ስልጣን የሚበቁ አመራሮች ተለይተው ታውቀዋል።
ከግምገማ በኋላ ብዙዎቹ አመራሮች የተስፋ መቁረጥ ስሜት ፊታቸው ላይ በግልጽ ሲነበብ፣ የተሻለ ውጤት የተሰጣቸው ጥቂት አመራሮች ደግሞ ከወዲሁ ደስታቸው የተለየ እንደነበር እየገለጹ ነው፡፡
በግምገማም ወቅት አመራሮች እርስ በርስ ይመወነጃጀሉ ከባድ ቃላትንም የውራወሩ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡። ግምገማው በለያየ ቅርጽና ይዘት በሌሎች አካላት ላይ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በሃዋሳ እንዲቀጥል እቅድ
ተይዟል።

No comments:

Post a Comment