Tuesday, January 19, 2016

ዜና ከደቡብ ኢትዮጵያ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የከተማ ታክሲዎችን ጨምሮ የህዝብ ማመላለሺያ ተሽከርካሪዎች ከትላንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።

መንግስት በአሽከርካሪዎች ላይ ያወጣው አዲስ መመሪያን ተከትሎ በተነሳ ቁጣ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የስራ ማቆም አድማ መምታቸውን ለኢሳት ከአከባቢው የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ከትላንት ጀምሮ ምንም አይነት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሆሳዕና መግባትም መውጣትም እንዳልቻለ በአድማው የተሳተፈ አንድ አሽከርካሪ ገልጿል። ከወራቤ ወደ ሆሳዕና 16 ሰዎችን ጭኖ ሲያመራ የነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላሺያ ተሽከርካሪ በአድመኞቹ ጥቃት ተሰንዝሮበት እንደወደመ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። አድማውን ህዝቡ እየተቀላቀለው እንደሆነ ተገልጿል። ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱንም ለማወቅ ተችሏል።

Source : https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1083286248370123&substory_index=0&id=112106198821471

No comments:

Post a Comment