Tuesday, April 7, 2015

ገዢው ፓርቲ የጦርነት ያክል ዘምቶብናል ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ተናገሩ


መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ በቀለ  እንደተናገሩት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ድርጅታቸው በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች እጩዎችን ቢያሰማራም፣ እጩዎቹ እየታሰሩና
እየተደበደቡ በመሆናቸው መድረክ ቀጣዩን ሂደት ለመወሰን እየተነጋገረ ነው።
አቶ በቀለ በሆድሩ ጉድሮ አባሎቻቸው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸውን፣ በሜታ ሮቢ  ከ50 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸውን፣ በግንደበረት የወረዳው አስተዳደር ሽጉጥ በማውጣት  አባሎችን ማስፈራራታቸውን ፣ ግንጭ ላይ ጽ/ቤታቸው መሰበሩን እና ሌሎችንም
እየደረሱባችው ያሉትን ችግሮች ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድም ሆነ ፖሊስ መልስ ሊሰጡዋቸው እንዳልቻሉ የገለጹት አቶ በቀለ፣ ጥቃቱና ዘመቻው የማይታገስ ከሆነ መድረክ ስለሚወስደው እርምጃ እየተነጋገረ ነው ብለዋል።
የፊታችን ግንቦት የሚደረገው ምርጫ አለማቀፍ ትኩረት አልሳበም። የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የካርተር ማእከል ምርጫውን እንደማይታዘቡ ይታወቃል  ገዢው ፓርቲ አንጻራዊ የሆነ ፉክክር ከሰማያዊ ፓርቲ እና ከመድረክ ይገጥመዋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በድርጅቶች ላይ
የሚደረሰው ጫና ብዙዎች ነጻ ምርጫ ይካሄዳል ብለው ተስፋ እንዳይጥሉ አድርጓቸዋል።

source: ethsat.com

No comments:

Post a Comment