Thursday, September 17, 2015

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመብራት መቆራረጥ አስቀራለሁ ብዬ ያሰብኩት ያልተሳካው በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ብድር ስላላገኘሁ ነው አለ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው 2007 የመብራት መቆራረጥን ለመቀነስ በከፍተኛ ደረጃ እሰራለሁ ብሎ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ የማከፋፈያ ጣቢያዎቹን አቅም የማሣደግ እና የማስተላለፊያ ጣቢያዎችን የመጠገን ሥራ እንደሚሰራ ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ለእነዚህ ስራዎች ማከናወኛ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ አንድ ቢሊዮን ዶላር በብድር አገኛለሁ ብሎም ተስፋ አድርጐ ነበር፡፡

ይሁንና ብድሩ ሳይገኝ መቅረቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የውጪ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ተፈራ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው በዚህ ዓመት ሌሎች አማራጭ የገንዘብ ምንጮች በመፈለግ የማከፋፊያ ጣቢያዎቹን አቅም የማሣደግ እና የማስተላለፊያ ጣቢያዎችን የመጠገኑ ሥራ ይሰራል ብለዋል፡፡

አምናም ቢሆን ብድሩ ባለመገኘቱ በኤሌክትሪክ ማከፋፊያ እና ማስተላለፊያ ጣቢያዎች ላይ ምንም አይነት ሥራ አልተሰራም ማለት እንዳልሆነ አቶ ገብረእግዚአብሔር ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም 19 የማከፋፊያ ጣቢያዎችን አቅም የማሣደግ እና የጐላ ችግር የነበረባቸውን በርከት ያሉ የማስተላለፊያ ጣቢያዎች የመጠገን ሥራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

የተጠየቀው ብድር ከዚህ በኋላስ ሊገኝ ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት ኃላፊው ይህ በእኛ ሳይሆን በሌሎች የመንግስት አካላት የተያዘ ስለሆነ ሊገለፅ የሚችለውም በእነሱ በኩል ነው ሲሉ መልሰውልናል፡፡

Source : https://m.facebook.com/photo.php?fbid=10154232228269616

No comments:

Post a Comment