Friday, November 6, 2015

Habtamu ayalew was in solidarity confinement for four months

ቶ ሀብታሙ አያሌው ለአመራሩ እንደገለፁት በማእከላዊ በእስር ላይ በቆዩባቸው አራት ወራት ከእስረኞች ተነጥሎ ለብቻው በጨለማ ክፍል ውስጥ እንደታሰረና ከሌሎች በተለየ ወደ መፀዳጃ እንዳይሄድ ይከለከል እንደነበረ፤ ከፍተኛ ድብደባ በተደጋጋሚ እንደተፈፀመበት ገልጧል፡፡

በተጨማሪም እንደተናገረው ምርመራ ያካሂዱበት የነበሩት ከፌደራልና ከደህንነት የሚመጡ ሲሆኑ ከሌሊቱ 6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት እያሰቃዩ ‹‹የግንቦት ሰባት አባል መሆንህን እመን፤ የፓርቲው ጠንካራ አመራር እነማን እንደሆኑ አውጣና የፓቲውን የፋይናንስ ምንጭ ግለፅ›› የሚሉ እንደነበሩ ተናግሯል፡፡

ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው ታስሮበት የነበረው ክፍል ቀዝቃዛ በመሆኑና ወለል ላይ እንዲተኛ በመደረጉ ለእግርና ለተለያዩ በሽታዎች ተጋልጧል፡፡ አመራሩ አይቶ እንዳረጋገጠውም ሲመጣ እያነከሰና ተደግፎ ሲሆን አስቸኳይ ህክምና የማያገኝ ከሆነ ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት እንደሚጋለጥ ተናግሯል፡፡

ሐብታሙን ‹‹የግንቦት 7 አባል ነኝ ብለህ ፈርም›› በማለት በተደጋጋሚ እያሰቃዩ የጠየቁት ሲሆን ያልሆንኩትን ነኝ አልልም በማለቱ ቴክኒካል የሆነ የአካል ጉዳት እንደሚያደርሱበትና ጭንቅላቱንና አንገቱ ስር በመደብደብ ተዝለፍልፎ እንዲወድቅ መደረጉንና ‹‹እስቲ አንድነት ያስፈታህ!›› በሚል እንደሚዝቱ ለሉዑኩ ተናግሯል፡፡

Source:https://m.facebook.com/jomanex/posts/10207461255307511

No comments:

Post a Comment