በPhillip Socrates
የቅማንት ህዝብ የነጻነት ትግል ጉዞውን ከጀመረ ብዙ ዓመታት አሥቆጥሯል፡፡ ለትግሉ ካነሳሱት ብዙ ጉዳዮች መካከል በልማትና ማንኛውም መሠረተ ልማት አድሎ ስለተፈፀመበት፤ በማንነቱ እንዲሸማቀቅ ስለተደረገ፤ የራሱን ባህል፣ ቋንቋና ሥነ-ልቡና እንዳያሳድግ ስለታፈነ፤ ይልቁንም ቅማንት የለም ተብሎ ከሀገሪቱ ሕዝብ ቆጠራ ስለተሰረዘ እና የመሳሰሉትን ማንሳት ይቻላል፡፡ ጥያቄው በተደጋጋሚ ለክልል 3 መንግሥት ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ሻጥሮችን በመሥራት ሕገ-ምንግሥት መሠረት ያለው ሕዝባዊ ጥያቄ እንዲጓተት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ አንድ ጊዜ “ቅማንት የለም” ሲሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ “ቅማንት የለም አላልነም ነገር ግን አማራ ሆኗል” በማለት፤ እንዲሁም “ቅማንት የራሱ ቋንቋ የለውም ስለዚህ አንፈቅድም” ብለውናል፡፡ በመካከል የፌደራል መንግሥታችን ጉዳዩን ለመፍታት በተዘጋጀበት ወቅት የክልሉ መንግሥት “ብአዴን ነው የቅማንትን ጥያቄ መመለስ ያለበት፤ ራሴን ገምግሜያለሁ” በሚል በቀጣፊ ምላሱ የፌደሬሽን ምክር ቤቱን አታሎ ጉዳዩን ወደ ራሱ አምጥቶታል፡፡ የቅማንት ሕዝብም “ጥያቄው ይፈታ እንጂ ችግር የለውም” በሚል ሕዳር 25 ቀን 2007 ዓ. ም ጎንደር ላይ ገዱ አንዳርጋቸው በጠራው ስብሰባ ላይ ተስማምቶ ወቷል፡፡ በወቅቱ ገዱ እንዳርጋቸው መርዝ በተመላ አፉ ዲሞክራት የሆኑ ቃላትን በማዥጎድጎድ የቅማንት ሕዝብ ጥያቄ በሰለጠነ አግባብ እንደሚፈታ ቃል ገቶ ተማምሎ ወቷል፡፡ ነገር ግን የክልል 3 ምክር ቤት “ቅማንት በ42 ቀበሌ ብቻ ራሱን እንዲያስተዳድር ፈቅደናል” በማለት የትምክህተኝነት አቋሙን ይፋ አድርጓል፤ ለቅማንት ህዝብ ያለውን የመረረ ጥላቻና ንቀት አሳይቶናል፡፡
ከዚህ በመነሳት የቅማንት ጨዋ ሕዝብ ጉዳዩን ለፌደሬሽን ምክር ቤት በማቅረብ ይግባኝ ብሏል፡፡ ይግባኙን የተቀበለው የፌደሬሽን ምክር ቤትም የሀገሪቱ ሕገ-ምንግሥት አንቀጽ 39 በያዛቸው ድንጋጌዎች መሠረት ጉዳዩን በሰፊው ካጠናና ከገመገመ በኋላ የቅማንት ሕዝብን ሕገ-ማንግሥታዊ፤ ሕዝባዊና ዴሞክራሲያዊ የማንነትና የራሥ አስተዳደር ጥየቄ በትክክል መልሷል፡፡ ነገር ግን የክልሉን መንግስት እንደ ትክክለኛ የመንግሥት ተቋም በመቁጠር (ከቅንነት) የቀሩትን ቀበሌዎች አካቶ መመለስ “ክልሉ እስካሁን ከመለሰው መልስ ስለማይከብድበት ክልሉ ጉዳዩን ይፈጽመው” በሚል ጉዳዩ ወደ ክልል 3 መጥቶ እንዲፈጸም ተርጓል፡፡ ይህ በተደረገ ማግስት ግን ገዱ አንዳርጋቸው ለአበልጁና የሙስና ጓዱ ግዛት አብዩ ባስተሳለፈው ቀጭን ትእዛዝ መሰረት የቅማንትን የማንነትና የራስ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ በደብዳቤ አፍርሷል፡፡ በቀጥታም ኮሚቴ አባላትን ማሳደድና ማሰር ብሎብ መግደል ጀምሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባለፈው ሰኔ ወር አይከል ከተማ ገቢያ ላይ ነብሰ ገዳይ የልዩ ሐይል ወታደሮቹን በማሰለፍ ከ6 በላይ ንጹሃን የቅማንት ልጆችን አስረሽኗል፤ አያሌ የቅምንት ተወላጆችን ቅማንት በመሆናችው ብቻ ከሥራ ገበታቸው አባሯል፡፡ ብዙዎችን አስሮ አሰቃይቷል፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ የክልሉን ውሳኔ ካልተቀበላችሁ ልክ እናስገባችኋለን እያለ ሲያስፈራራና ሲያሸብር ከርሟል፡፡ ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለው ከእስር ሸሽተው በጫካ የተደበቁትን የኮሚቴ አባላት ለመግደልም ያልፈነቀለው ጉድጓድ አልነበረም፡፡ ይሁንና “የቅማንት ሕዝብ እንደ ሕዝብ ካላተጨፈጨፈ ውሳኔያችን አይቀበልም” በሚል ሰይጣናዊ ውሳኔ ተነሳስቶ ከጥቅምት 24/2008 ዓ. ም ጀምሮ በቅማንት ሕዝብ ላይ ግልጽ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አውጆ በተለያዩ አቅጣጫዎች እስከ አፍንጫው የታጠቀ ልዩ ሐይሉን አዘመተ፡፡ የዘመቻው መጠሪያም “ዘመቻ 42” ይባላል፡፡ ይህ ቅማንትን የማጥፋት ዘመቻ የጎንደር ህብረት በሚባለው ጸረ-ቅማንት የትምክህተኞች ድርጅት የንዘብ ድጋፍ የሚታገዝ ነው፡፡ ይህ ጸረ-ቅማንት ድርጅት ገዱ እንዳርጋቸው፣ ግዛት አብዩ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር እና ቡችሎቻቸው ቅማንትን ደምስሰው የቀረውን በ42 ቀበሌ ወስነው ካስቀመጡትና ልክ ካስገቡት የ2.5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ በመሆኑም “ዘመቻ 42” ለትምክህተኞች ከፊት ለፊታቸው የተከመረውን የዶላር ክምር ብቻ እያዩ ቅማንትን እንዲረግጡ የታቀደ ዘመቻ ነው፡፡ ይሁን እና ዘመቻው የቅማንት ሕዝብን አቅምና ጀግንነት በመረዳል ላይ የታቀደ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ ዘመቻ የቅማንትን ሕዝብ በ2.5 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ አባቶቻቸው ሲያደርጉት እንደነበረው የድንቁርና ሥራ በቅማንት ላይ ለመሥራት ተመሙት፡፡

የመጀመሪየው ሙከራ በጮንጮቅ በኩል አልፎ እየገደለ ጋባ ጋላገርን እንዲያጠቃ ነበር፡፡ ነገር ግን እቅዱን ቀድሞ የተረዳው የቅማንት ገበሬ ጨንጮቅ ላይ ራሱን ተከላክሎ በትምክህተኛው ላይ የማያዳግም ርምጃ ወስዶበታል፡፡ ትምክህተኛው ይህን ሽንፈት ሲመለከት ያለ የሌለ ሐይሉን ከተለያዩ የክልሉ ዞኖች ማለትም ከደብረታቦር፣ ከሰ/ጎንደር፣ ከደብረብርሃን፣ ከማርቆስ፣ ከደሴ ወዘተ በማሰባሰብ በጎንደር በኩል ወደ ሮቢት አዝምቷል፡፡ ነገር ግን የቅማንት ጀግኖች ማውራ ላይ አድፍጠው በመጠበቅ ያቀደውን ጥፋት ከመፈጸሙ በፊት አፍነውታል፡፡ የማውራው ውጊያ ለረጅም ቀናት የዘለቅ ሲሆን እስከ 29/02/2008 ከቀኑ 7 ሠዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ውጊያ ከተሰለፈው የትምክህተኛው ሐይል ከ50 በመቶው በላይ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል፡፡ ከጀግኖቹ የቅማንት ገበሬዎች መካከልም የተወሰኑ ተሰውተዋል፡፡ ትምክህተኛው ውጊያውን ያከሄደው በፌደራል መንግሥቱ ተደብቆ ስለሆነ ቁስለኛውን ለላፉት 3 ተደታታይ ቀናት ወደ ጎንደር ሆስፒታል እንዳይመጡ ደብቆ ወደ ሌላ ቦታ ሲያጓጉዝ ሰንብቶ ዛሬ ግን ጎንደር ሆስፒታለ የተወሰኑ ቁስሎኞችን አስገብቷል፡፡ እነዚህ ቁስለኞች እንደሚሉት ከሆነ ገበሬው ከየት መጣ ሳይባል በተያዩ አቅጣጫዎች በመምጣት ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ነው፡፡ ቦታው ድረስ በመሄድ ይህን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ይህን የክልሉን ወንጀል የተረዳው የፌደራል መንግሥት ጦረነቱን ለማስቆም ወታደር ልኳል፡፡ በዚህ ምክንያትም በማውራ በኩል የነበረው ጦርነት አቁሟል፡፡ ይሁን እንጅ በደረሰበት ከፍተኛ ሽንፈጽ የተበሳጨው የትምክህተኞች አለቃ ገዱ አንዳርጋቸው ያመለጠውን ዶላር ለማስመለስ ጦርነት አቁሜያለው ካለ በኋላ ማውራ ከባቢ በሚገኙ መንደሮች ላይ መንደር ለመንደር እየተዘዋወሩ ሕጻናትንና ሴቶችን ገድለው እንዲወጡ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ወታደሩ ወደኋላ ሲመለስ ያገኘውን እየገደለ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ እንስሳትን በጥይት እየመታ ገድሏል፡፡ ዓላማው ቅማንትን ማጥፋት ስለነበረ ማንኛውም ቅማንት የተባለን ፍጥረት መገደል አለበት ብሎ ወስኗል፡፡ ይህ ሁኔታም ፌደራል በመግባቱ ምክንያት ለሠላም ቅድሚያ የሰጠውን የቅማንት ገበሬ መልሶ እንዲዋጋ እያደረገው ነው፡፡ ጀግኖቹ አሁንም የጥቃት እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል፡፡ ለዚህ ጨካኝ አረመኔ የገዱ አንዳርጋቸው እጅ መንጠት የለም የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡
ይህን ሁሉ የጭካኔና የእብደት ሥራ የሚሰራው የክልሉ መንግሥት መሳይ ጸረ ሕገ-መንግሥት ሀይል እንደ ሽፋን የሚጠቀመው “ግንቦት 7 ከቅማንት ጎን ተሰልፎ እየወጋኝ ነው” እያለ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል ቀደም ሲል “ሕወሓት ነው የልብ ልብ የሰጣችሁ” እያሉ ሲያስወሩና ሲያራግቡ ከቆዩ በኋላ አሁን ደግሞ ግንቦት 7 ማለታቸው እየሠሩት ያለው ወንጀል ምን ያክል ዓይን ያወጣ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ለመሆኑ በርእዮተ ዓለም ደረጃ ስንመለከተው ግንቦት 7 የሚስማማው ከክልል 3 ትምክህተኞች ጋር እንጅ ሕገ-መንግስቱን ከለላ ካደረገው የቅማንት ሕዝብ ጋር አይደለም፡፡ ቅማንት የህገመንግሥቱን አንቀጽ 39 ሙሉ በሙሉ የተቀበለና በዚህም መሠረት መብቱ እንዲከበርለት የሚታገል ቅን ሕዝብ እንጂ ትምክህተኛ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከግንቦት 7 ጋር በምንም መንገድ ግንኙነት ሊፈጥር ወይም ሊጋባ አይችልም፡፡ መቸም “በገበሬ ተሸነፍኩ” ላለማለት የዘየዷት መላም ትመስላለች፡፡ የሚዋጋውን ገበሬ ትቶ መንደር በመዝለቅ እንስሳትንና ሕጻናትን ማረድ ሽንፈትንና ጭፍንነትን የሚያሳይ እንጂ ጀግንነት አይደለም፡፡ በእርግጥም ቅማንት እውነትን እለያዘ በያዘው ኋላ ቀር ጠምንጃ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን የገዱን ጦር አርበድብዶታል፡፡ እርግጥ ነው የሞቱት ትምክህተኞች ሳይሆኑ ውሾቻቸው ናቸው፡፡ ይህን ያሳዝናል፡፡ ቅማንት ህልውናውን የሚከላከልበት ሌላ አማራጭ አልነበረውም፡፡
በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የዓለም ማህበረሰብ የክልል ሦስት ትምክህተኛ መሪዎች በቅማንት ሕዝብ ላይ እያደረሱት ያለውን ግፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመረዳት ከጎናችን እንድትሰለፉ እንጠይቃለን፡፡ አንዲት መንግሥት ካላት ሀገር እንዲህ ዓይነት ወንጀል ሲፈፀም ማየት እጅግ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ይህን መልዕክት ለመላው የዓለም ሕዝብ በማስተላለፍ ለቅማንት ሕዝብ ያላችሁን አጋርነት እንድታሳዩ እንጠየቅን የፌደራል መንግሥታችን ያደረገውን አፋጣኝ እርምጃ እያደነቅን በቀጣይም የቅማንትን ሕዝብ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እንሚመልስልንና አትምክህተኛ የክልል 3 መሪዎች ጭቆና የቅማንትን ሕዝብ ነጻ እንደሚያወጣው እርግጠኞች ነው፡፡

አማራነት ማንነት እንደሆነ ሁሉ ቅማንትነትም ማንነት እንጂ ወንጀል አይደለም!
ድል ለጭቁን ሕዝቦች!
No comments:
Post a Comment