Friday, November 6, 2015

እነ መሳይ ትኩ ለህዳር 14 ተቀጠሩ * እስማኤል ዳውድ መከላከያ ምስክሮቹን አሰማ



ኢዩኤል ፍሰሀ ዳምጤ እንደዘገበው

በ2001 ዓ.ም የወጣውን የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 7/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፤ የሚል ክስ በፌደራል አቃቤ ሕግ በኩል የቀረበባቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ መሳይትኩና 2ኛ ተከሳሽ ሰጠኝ ሙሉ ተለዋጭ ቀጠሮተሰጣቸው፡፡

ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማድመጥ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበሩት መሳይ ትኩና ሰጠኝ ሙሉ ምስክሮቻቸውን ሳያሰሙ ለ5ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በማስመልከት 1ኛ ተከሳሽ መሳይ ትኩ፣ ለፍ/ቤቱ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡ ‹‹የተከበረው ፍ/ቤት እኛም ሃሳብ አለን››በሚል በስሜት ተውጦ የተናገረው መሳይ፣ ከጥቅምት 16 ቀን ጀምሮ ምስክሮችን ለማድመጥ ተደጋጋሚ ቀጠሮ እየተሰጣቸው እንደሚገኝ፣እስካሁን ድረስም ምስክሮች ባለመደመጣቸው የተነሳ ከክፍለ ሀገር የሚመጡት ቤተሰቦቻቸው ላይ እንግልት እየደረሰ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡ በዕለቱ በችሎቱ የተሰየሙት ዳኛ ምስክሮች ተሟልተው እስኪቀርቡ ድረስ መታገስ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ‹‹በእኔ ላይ አቃቤ ሕግ ሊያሰማው ያዘጋጀው ምስክር በፍ/ቤት ውስጥ አይቼዋለሁ›› በማለት ለችሎቱ ያስረዳው መሳይ፣ ምስክሩ እንዲደመጥልኝ ሲል ፍ/ቤቱን ጠይቋል፡፡ አቃቤ ሕግ በበኩሉ ‹‹ምስክሩ አልቀረበም›› በማለት ለፍ/ቤቱ ሲናገር ተደምጧል፡፡ ፍ/ቤቱ አቃቤ ሕግ ምስክሮቹን አሟልቶ እንዲያቀርብና ምስክሮቹን ለማድመጥም ተለዋጭቀጠሮ ለህዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡

አቃቤ ሕግ በመሳይ ትኩ ላይ አንድ ምስክር ያዘጋጀ ሲሆን፤ በሁለተኛ ተከሳሽ ሰጠኝ ሙሉ ላይ ደግሞ ሁለት የደረጃ ምስክሮችን እንዳዘጋጀ ለመረዳት ተችሏል፡፡ አቶ መሳይም ሆነ አቶሰጠኝ ከየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በሌላ ዜና፣‹‹ስብሰባንበማወክ›› ወንጀል ተከሶ ላለፉት 6 ወራት ክሱን በማረሚያ ቤት ሆኖ እየተከታተለ የሚገኘው፤የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አባል ወጣት እስማኤል ዳውድ፣ በትላንትናው እለት መከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ እስማኤል፣ የቀረበበትን ክስ በሚመለከት ለመከላከል ይረዱኛል ብሎ ያሰባቸውን ሁለት ምስክሮች ያስደመጠ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱ ብይን ለመስጠት ለህዳር 7 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ መንግስት አይኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት ‹‹ስብሰባንአውከሃል›› የሚል ክስየቀረበበት እስማኤል፣ ከሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

The post እነ መሳይ ትኩ ለህዳር 14 ተቀጠሩ * እስማኤል ዳውድ መከላከያ ምስክሮቹን አሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Source:: Zehabesha

No comments:

Post a Comment