ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት መስተዳድሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ያወጣውን ህግ የተቃወሙ አሽከርካሪዎች የ3 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ በሁዋላ፣ የተወሰኑ አሽከርካሪዎች ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አሽከርከሪዎች እንደሚሉት ፣ ወደ እስር ቤት ከተወሰዱ በሁዋላ ጨማቸውን አውልቀው፣ እጆቻቸው በሲባጎ ገመድ ወደ ሁዋላ ታሰሮ የወስጥ እግራቸውን ተገርፈዋል።
ምንም እንኳ አሽከርካሪዎቹ በግዴታና በቅጣት ስራቸውን እንዲጀምሩ ቢደረግም፣ አንዳንዶች ግን እስር በመፍራት ከአካባቢው እርቀዋል። ብአዴን 35ኛ አመቱን ለማክበር ሸር ጉድ በሚልበት ሰአት አድማው በመካሄዱ የተበሳጩት ባለስልጣናት ፣ በበአሉ ቀን አሽከርካሪዎች አድማ ሊያደርጉ ይችላሉ ብለው በመስጋት ከአሁኑ የክትትል ስራ እየሰሩ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment