dr shiferaw tekelamariam
በዛሬው እለት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሶስት ሚኒስትር ዴታዎች እንደተመደቡለት በዛሬው እለት ይፋ ተደርግዋል
(ሰበር ዜና ቢቢኤን) በአዲሱ የመንግስት መዋቅር የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስት መስሪያ ቤት በሁለት የተከፈለ ሲሆን የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትር መስሪያ ቤትና ፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር በሚል ነው የተዋቀረው፡፡ የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ሁነው ሲሾሙ ዶክተር ሽፈራው ደግሞ ፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ሁነው ተሹሞዋል፡፡
በዛሬውዶክተር ሽፈራው በሚኒስትርነት የሚመሩት ፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታዎች እንደተሾሙለት መንግስት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት ፡፡ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን በድጋሜ ተሹመዋል፡፡
ከአቶ ሙሉ ጌታ ውለታው በተጨማሪ አቶ አወል አርጊሶ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የብዙሃን፤ የሙያ ማህበራትና የሃይማኖቶች ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን፤ አቶ ካይዳኪ ገዛሀኝ በፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የታዳጊ ክልሎችና የአርብቶ አደር ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ከዚህም መረዳት እንደተቻለው አሁንም የሃይማኖት ጉዳዮችን በተመለከተ በዋናነት የሚመራው የህወሃት ኢህአዴግን ተልኮ ከማስፈጸም ባሻገር ለኢስላም ጥላቻ እንዳላቸው በሚነገርላቸው በዶክተር ሽፈራው አማካኝነት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዶክተር ሽፈራው በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የአህባሽ አስተሳሰብን በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለመጫን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን አሁንም በዚሁ መስሪያ ቤት አማካኝነት ይህን እኩይ ስራቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ መንግስት በሃይማኖት የሚያደረገውን ጣልቃ ገብነት ሲታገል መቀየቱ የሚታወቅ ነው፡፡
The post ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም አሁንም የሃይማኖት ጉዳዪችን በበላይነት በሚኒስትርነት የሚመሩት እርሳቸው መሆናቸው ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.
Source:: Zehabesha
No comments:
Post a Comment