Tuesday, October 6, 2015

ከሳቂታነት ወደ እንቅልፋምነት


የኢህኣዴግ ፖርላማ ራሱን ከሳቂታነት ወደ እንቅልፋምነት አሸጋግረዋል።
ከትግራይ ክልል በኔትወርክ ኣማካኝነት ኣራት ኪሎ የገቡት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምልምሎች ኣዳራሽ የገቡት የህወሓት ኣባላት እንዲህ በእንቅልፍ ጭልጥ፣ ለሽ ብለው ተኝተው ኣሃዱ ብለው ስብሰባቸው ጀምረውታል።
በክልሉ የድርቁ ኣደጋው በመስኖ ኣማካኝነት የተመረተው 75 ሚልዮን ኩንታልና በዝናብ 38 ሚልዮን ኩንታል ምርት ስላለ ተረረጋግተው ለመተኛት ችለዋል።
ሽግግሩ ቀድመው የጀመሩት ከትግራይ ክልል ተወክልው የሄዱት የተከበሩ ወይዘሮ ኣስቴር ኣማረ ናቸው።
ሳቂታው ፖርላማችን በGTP-2 እቅድ መሰረት ወደ እንቅልፋምነት መሸጋገሩ ኣሳይተዋል።
በእውነት ወከለኝ ያሉት ህዝብ በድርቅ ኣደጋ ኣጣብቅኝ ውስጥ እያለ እንዲህ በእንቅልፍ ጭልጥ ብሎ መተኛት ምን ይባላል?
በነገራቹ ላይ ወይዘሮ ኣስቴር ኣማረ በድርቅ ክፋኛ ከተመታው እንደርታ ወረዳ ተወክለው ፖርላማ የገቡ ናቸው።
በእግሪሓሓሪባ፣ ኣሸጎዳ፣ ዳ ማርያም ዳሓን ወዘተ ከፍተኛ የህዝብ ጥያቄ ያለው ህዝብ ኣንድም ቀን ችግሩ በሰላም ለማስፈታት ያልሞከሩና ከ2002 ዓ/ም ጀምረው የተወከሉ ናቸው።
ትናንት በረሃብ የሞቱት 3 ወገኖች ብያ የፃፍኩትም እሳቸው ከተወከሉበት ወረዳ ናቸው።
የንፀውይይ………!




















No comments:

Post a Comment