መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጠዋት በሳሸመኔ ተክለሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን መቅደስ ውስጥ ካህናትና ዲያቆናት እርስ በርስ በመደባደባቸው ሰዎች ተገድተዋል።
የግጭቱ መንስኤ የቆየ መሆኑን የሚናገሩት ምእመናኑ ዛሬ የተፈጠረው ድርጊት ግን ያልተጠበቀ ነው። ካህናቱ ጎራ ለይተው መደባደባቸውን ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎአል።
ኢሳት ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ባይችልም፣ በሰአቱ የተኩስ ድምጽም ተሰምቷል። ጥይቱን ማን ተኮሰው የሚለው ጥያቄ የከተማው መነጋገሪያ ሆኗል።ከዚህ ቀደም ቀኖናንና አስተዳደር በተመለከተ የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ ጳጳሱ የሰጡት መፍትሄ ለውዝግቡ መነሻ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ምእመናን ይናገራሉ። ቤተክርስቲያኑዋን የህዝብ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በቤተከርስቲያን ሃላፊዎች እንዳልተወደደም ምእመናን አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment