Tuesday, July 21, 2015

የነአብርሃ ደስታ ክስ መከላከያ ውድቅ ተደረገ • ለነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥረዋል


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ዘላለም ወርቃገኘው የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው ተከሳሾቹ ሀምሌ 1/2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት 7/2006 ዓ.ም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተገኘ የተባለ መረጃ ከአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ማስረጃ ዝርዝርነት እንዲወጣ፣ ተከሳሾቹ ለፖሊስ መረጃ የሰጡበት መንገድና ፖሊስ የሰነድ ማስረጃዎችን የያዘበትን መንገድም አቃቤ ህግ ህጋዊ መሆኑን ስላላረጋገጠ በደንበኞቼ ላይ በማስረጃነት እንዳይያዝ ሲሉ መቀወወሚያ አቅርበው ነበር፡፡

ከተከሳሾቹ መካከል በዛሬው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹መቃወሚያው የቀረበው ከተከሳሾች እጅ ተገኙ የተባሉት ማስረጃዎች በህጋዊ መንገድ የተገኙ ስለመሆናቸው አቃቤ ህግ በማስረጃ ስላላረጋገጠ ነው›› ሲል ፍርድ ቤቱ መቃወሚያውን እንዲቀበለው ጠይቋል፡፡ ሆኖም ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መቃወሚያውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በነፃ ይሰናበቱ ወይንም ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ለብይን ለነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም 9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ ከጥብቅና በመታገዳቸው ምክንያት ሰባቱም ተከሳሾች በዛሬው ችሎት ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡ በዚህ መዝገብ ተከሰው አቶ ተማም መቃወሚያ ካቀረቡላቸው መካከል አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሽ ይገኙበታል፡፡

Source:: Zehabesha

No comments:

Post a Comment