Monday, August 10, 2015

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደብዩብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተደራዳሪን ከአገሯ አስወጥታለች።

እርመጃው የተወሰደው የደቡብ ሱዳን መንግስት አንድ የተቃዋሚ አባል ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄድ ማገቱን ተከትሎ ነው። ደቡብ ሱዳን የድርድሩ ቦታና አደራዳሪው ስዩም መስፍን እንዲቀየር የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ የሰጡት ምክንያትም፣ አዳራዳሪዎቹ ራሳቸው በአገራቸው የተቃዋሚ ሃይሎችን ያስተናግዳሉ፣ እነሱ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሳይሆኑ እኛን ሊሸመግሉ አይችሉም የሚል ነው። የደቡብ ሱዳን መንግስት የተቃዋሚዎችን ወኪል ተደራዳሪ ላም አኮልን ለድርድር ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄዱ እገዳ በጣለ ማግስት፣ አዲስ አበባ ለድርድር ሄደው የነበሩት የካቢኔ ሚንስቴሩ ማርቲን ኤሊያ ላሙሮ በተመሳሳይ መንገድ ተባረዋል። ኤሊያና ቡድናቸው ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የሄዱት መንግስትን በመወከል የሰላም ስምምነቱ ላይ ለመወያየት ነበር።ነገርግን አኮል የሚመሩት የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቡድን በረራቸው ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በፕሬዚዳንት ሳልፋኪር ትእዛዝ እንዳይጓዙ ተከልክለዋል። ኤሊያ " ኢጋድ ከሳልፋኪር መንግስት ጋር ችግር አለበት። የሰላሙ ድርድር በአፋጣኝ ታንዛኒያ፣ሩዋንዳ አሊያም ደቡብ አፍሪካ መደረግ አለበት" ብለዋል። አሁን የእኛ መደምደሚያ ሃሳብ በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ የኢጋድ አደራዳሪዎች ቡድን እንደገና መዋቀር አለበት ኬንያዊው ዊሊ እና ጄኔራል ላዛሩ ሲምቢዮ ተቀባይነት ሙሉ ለሙሉ አላቸው። ኢትዮጵያዊው ስዩም መስፍንና ሱዳናዊው መሃመድ አህመድ ግን የግድ በ አፋጣኝ በሌላ መተካት አለባቸው በማለት ተናግረዋል።
Source :http://ethsat.com/amharic/%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%88%b1%e1%8b%b3%e1%8a%95-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%8b%b5%e1%88%a9-%e1%8a%a8%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0/

No comments:

Post a Comment