መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን “አባ ሰንጋ” የተሰኘው የከብቶች በሽታ ተከስቶ በርካታ ሰዎችና ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን እንዳጠናቀረው መረጃ እስካሁን በበሽታው አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። በበሽታው እጅግ በርካታ ከብቶች እያለቁ በመኾናቸውም የ አካባቢው ህዝብ መጪውን የመስቀል በዓል ከስጋ ተዋጽኦ ውጪ እንዲውል ተገዷል።
በአሁኑ ወቅት ለተወሰኑ ከብቶች ክትባት መስጠት የተጀመረ ቢኾንም በሽታው በፍጥነት እየተዛመተ መኾኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። ከመስቀል በዓል ጋር ተያይዞ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት መፈጠሩንም ዘጋቢያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment