Thursday, August 27, 2015

የተቃዋሚ አባላትን እያደኑ ማሰሩ እንደቀጠለ ነው


ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ነሃሴ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ አብዮት ፋና ቀበሌ ሶስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸውን የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡
ሶስቱም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ቤታቸው በታጣቂ ተከቦ እንዳደረ የተገለፀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ታድነው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ተመስገን የኔሀብቴ፣ ማስተዋል አዱኛና ሙሉ አለየነው ሲሆኑ ሌሎች አባላትም እየታደኑ ነው ተብሏል፡፡
በዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የቀበሌ መታወቂያ ሲጠይቁ ‹‹የእኛ አባል ካልሆንክ አንሰጥህም›› እንደሚባሉ የጠቀሱት አስተባባሪዎቹ፣ አቶ ተመስገን የኔሀብቴ መታወቂያ በጠየቀበት ወቅት የቀበሌው ሊቀመንበር ‹‹የእኛ አባል ካልሆንክ መታወቂያ አልሰጥህም›› በማለታቸው፣ እሱም ‹‹መብቴ ነው!›› ብሎ በመከራከሩ ነሃሴ 11 ቀን 2007 ዓ.ም፣ እያስፈራራኝ ነው፣ ብለው እንዳሳሰሩትና ነሃሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. 1,500 ብር ዋስ አስይዞ ከእስር ተለቅቆ እንደነበር ተገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ በአርሲ በቆጅ የሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የተወዳደሩትና የሰርቦ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጃዋሩ ገልገሉ በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት የመንግስት አግልግሎት እንደማያገኙና በፖሊስ ተይዘው መታወቂያቸውን ተነጥቀዋል። ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ስለሆንኩ መታወቂያየን በግድ ነጥቀውኛል፡፡ ይህ የእኛ መታወቂያ ነው ምንም አታመጣም ሂድና ሰማያዊ ፓርቲ ይስጥህ!›› እንደተባሉ ጋዜጣው ዘግቧል።

Source :Esat

No comments:

Post a Comment