Thursday, August 27, 2015

በአዲስ አበባ ወረዳ 9 17 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ


ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በድንገት በመምጣት በጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌ 02 የሚገኘውን የንግድ ድርጅታቸውን አሽገውባቸዋል። “በቂ ምክንያት ሳይኖርና በቂ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጠን፣ ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ ስራ ፈተን ቤተሰቦቻችን ለችግር ተጋልጠዋል” በማለት የሚናገሩት ነጋዴዎች፣ ጉዳዩን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መፍትሄ የሚሰጣቸው አላገኙም።
የወረዳው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ወኪል የሆኑት አቶ ተክለአብ፣ ነጋዴዎቹ ራሳቸው እንዲሰሩበት የተሰጣቸውን ቦታ ለሶስተኛ ወገን አከራይተዋል በሚል ድርጅታቸው መታሸጉን አምነው፣ ተሰጠ የተባለው የማስጠንቀቂያ ጊዜ አጭር መሆኑን እንደሚያምኑ፣ ነገር ግን እስካሁን ሲሰራበት የነበረ አሰራር በመሆኑ ምንም ማድረግ እንደማይቻል ገልጸዋል።
ነጋዴዎቹና ቤተሰቦቻቸው ውሳኔ አጥተው ለአንድ ወር በላይ መጉላላታቸው ተገቢ ነው ወይ ተብለው ለተጠየቁት፣ ሃላፊው ተገቢ አለመሆኑንና ሌሎች አመራሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡዋቸው ግፊት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

Source :Esat

No comments:

Post a Comment