ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ በጋዛ ሰርጥ በሃማስ የታገተው ኢቲዮ እስራኤላዊ ወጣት አቭራም መንግስቱ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቹ ልጃችን ይለቀቅ በማለት በጋዛ ኤርዝ መተላለፊያን ዘግተው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን የልጃቸውን መታገት በዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲታወቅላቸውም ተማጽዕኖዋቸውን አሰምተዋል።
የአቭራም ወንድም ”እኛ በነፃነት የመዘዋወር መብትን እናከብራለን፣ ሁላችንም ፍልስጤማዊያንም እስራኤላዊያንም ጭምር እኔ አሁን የምንጠይቀው ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ወንድሜን ሃማስ እንዲለቅልኝ ብቻ ነው።” ብሎአል።
ሃማስ በበኩሉ የታጋቹ ቤተሰቦች ልጃቸው የዐዕምሮ ሕመም ችግር እንዳለበት ያቀረቡትን ተማጽኖ ግድ እንደማይሰጠው አስታውቋል።
ቤተ እስራኤላዊያን እስራኤል ውስጥ መድሎና መገለል እንደሚደርስባቸውና የእስራኤል መንግስት ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ያልተከታተለው በቆዳ ቀለሙ የዘረኝነት ሰለባ በመሆኑ ነው በማለት መናገራቸውን ዘ ጀሩሳሌም ፕሬስ አክሎ ዘግቧል።
Source : Esat
No comments:
Post a Comment