ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ከዝናብ እጥረት ጋር በተያያዘ በተነሳው ድርቅ በርካታ ገበሬዎች ለችግር የታገለጡ ሲሆን፣ ይህም ሳያንስ የዞኑ ካድሬዎች አርሶአዳሪው ህዝብ ማዳበሪያ በብድር በግድ እንዲወስድ እያስገገደዱት መሆኑ ችግሩን አባብሶታል። የዝናብ መጠኑ መዋዠቅ ገብሬውን በስጋት ላይ የጣለው መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ዝናብ ጭራሽ በመጥፋቱ አርሶአደሩ ለችግር ተጋልጦ የእርዳታ እህል በመጠባበቅ ላይ ነው። በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ዝናብ ከልክ በላይ በመዝነቡ ሌላ ጉዳት እያደረሰ ነው። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ማዳበሪያ ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አርሶደአሮችን፣ በተቃዋሚነት እየፈረጁ እስከማሰር መድረሳቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸውለታል።
Source :http://ethsat.com/amharic/%e1%89%a0%e1%8c%8b%e1%88%9e%e1%8c%8e%e1%8d%8b-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%89%85%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%b3%e1%89%a0%e1%88%aa%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8b%b3-%e1%8c%88%e1%89%a0/
"Democracy must be built through open societies that share information" Atifete Jahjaga
Press Freedom, Democracy and Human right
Thursday, August 13, 2015
በጋሞጎፋ ዞን ድርቅና የማዳበሪያ እዳ ገበሬውን ለስቃይ እየዳረገው ነው ተባለ
Labels:
Amharic News,
Ethiopia
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment