Thursday, August 27, 2015

የቀድሞዋ የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር /ሞንጆሪኖ/

አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ዘመን የካሳንቺሱን መንግስት ከመቀሌ አምጥተው የደባለቋት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር /ሞንጆሪኖ/ በንትርክ ላይ ባለው የሕወሓት ጉባኤ ላይ ነጥረው ወጥተዋል:: ዛሬ ወይም ነገ የሕዝብ ድምጽ ይሰጥበታል በሚባለው በዚሁ ጉባኤ ላይ አቶ መለስ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አድርጎ ያመጣት ሞንጆሪኖ ለትልቅ ቦታ ታጭታለች እየተባለ ነው:: ለመሆኑ ይህች ሴት ማናት?

ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ትርፉቶች በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ጽፏት ነበር:: ተጨማሪ መረጃዎች እስኪመጡ መልካም ንባብ::

የሞንጆሪኖ ለቅሶ…

በሰፈሩት ቁና ሆነና ነገሩ የሕወሓት መሰንጠቅ የሞንጆሪኖን ፍጹማዊ አገዛዝ እንዲያከትም አደረገው:: በ እርግጥ የተስፈማሪያምን ያህል ውግዝ ከማርዮስ አልደረሰባትም:: ከአቶ መለስ ተግሳጽ ውጭ::

አቶ መለስ እንዲህ አላት:-

“ሞንጆሪኖ አዲስ አበባን የለውጥ ማዕበል ውስጥ አስገብተሽ ታስተካክያለሽ ብለን ነበር የላክንሽ:: አንቺ ግን የድርጅቱን አደራ በልተሽ ከጀርባ ስታደራጂ ከረምሽ:: ኸረ ለመሆኑ ምን ጎድሎብሽ ነው? እነስዬን ስታውቂያቸው ቀርተሽ ነው; አብረሽ ድርጅቱ ላይ ገመድ ልታጠልቂ የነበረው?”

ሞንጆሪኖ ተንሰቅስቃ አለቀሰች:: ስጋ ስው አትን ጠርታ ሁለተኛ እንደማይለመዳት ቃል ገባች:: እግሩ ላይ ተደፍታ ይቅርታ ጠየቀች:: ከነተወልደ ጋር እንዲኤት እንደተመሳጠረች ዘከዘከች:: የህቡዕ እንስቃሴው ከስድስት ወር በፊት በአዲሳባ መጀመሩን አስረዳች:: በአዲስ አበባ ያሉት የዞን ሊቀመናብርት ትልቁ ሥራቸው መሆኑን ገለጸች:: ካድሬዎቹ አባዝተው ስለበተኑት ወረቀት ዘከዘከች:: አመናት::

ፊቱን ወደ እሷ አነሳ… ራራላት::

እንደቀድሞ ባሏ አባይ ጸሐዬ የምህረቱ ተቋዳሽ አደረጋት:: የዘመናዊ ዕውቀት ማነስ የፈጠረው ችግር ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ የቀለም ትምህርት እንድትማር ፈረንጅ ሃገር ሰደዳት:: ትምህርቷን አጠናቃ እንደመጣች ጓዟን ጠቅልላ መቀሌ ገባች:: የትግራይን ካቤኔ ተቀላቀለች:: ለአቶ መለስ ያላትን ታማኝነቷን በተግባር አሳየች:: እሱም ካሳውን በቁሙ ተቀበለ:: በዚህ ሳይወሰን በሕወሓት ሁለተኛ ትውልድ ውስጥ እንድትታቀፍ የመጀመሪያው ምርጫ አደረጋት::

(ሞንጆሪኖ ፈትለወርቅ ሆናለች:: የአዲሷ ፈትለ ወጣትነት የድሮዋ ሞንጆሪኖ ነው:: አፍታም ሳይቆይ የሕወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ ተካሄደ:: ፈትለወርቅ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነች::

(የመለስ ትርፉቶች መጽሐፍ ገጽ 56 – 57)

***

Source:: Zehabesha

No comments:

Post a Comment