ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢህአዴግ የድርጅት አባለት ግምገማ መጠናቀቁን ተከትሎ የግምገማ ውጤት እየወጣ ሲሆን፣ በዚህም ግምገማ መሰረት በርካታ የከተማዋ ወረዳ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ ታውቋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ከ50 በላይ አመራሮች ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ከ20 በላይ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ክ/ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ተገምግመው እጅግ ዝቅተኛ የሆነና በቀጣይ በኃላፊነት መቆየት የማይችሉበት የድርጅት ግምገማ ነጥብ ተሰጥቷቸዋል። ይህንን ተከትሎ ብዙዎች አባላቶች ተከፍተው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ሰርተፍኬትና ድፕሎማ ያላቸው ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አባላት በአመራርነት አይቀጥሉም የሚል አዲስ የግምገማ መስፈርት መጨመሩ፣ ብዙ የኢህአዴግ አባላትን አስክፍቷል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር 116 ወረዳዎች ሲኖሩ፣ እያንዳንዱ ወረዳ 15 በሹመት ደረጃ የተቀመጡ የጽ/ቤት ሃላፊ የድርጅት ካድሬዎች አሉት፡፡
Source :http://ethsat.com/amharic/%e1%8c%88%e1%8b%a2%e1%8b%8d-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2-%e1%89%a0%e1%88%ad%e1%8a%ab%e1%89%b3-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3/
"Democracy must be built through open societies that share information" Atifete Jahjaga
Press Freedom, Democracy and Human right
Wednesday, August 12, 2015
ገዢው ፓርቲ በርካታ የአዲስ አበባ የወረዳ አመራሮቹን ሊቀንስ ነው
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment