የቀድሞ የኢሕዴን እና ሕወሓት ታጋዮች በሰራዊቱ እና ደህንነቱ ውስጥ በወሽመጥነት ሊመደቡ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የወታደራዊውን ደርግን አገዛዝ ለመጣል በረሃ ገብተው ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉ በኋላ በተለያይ ምክንያቶች የአይናቸው ከለር ሳያምር ስለቀረ ብቻ ከኢሕአዴግ ሽምቅ ተዋጊ ሰራዊት የተባረሩ በካሳ ክፍያ ሰበብ በትንንሽ ጥቅማጥቅም ተጠልዘው እንዳልታገሉ ከመንገድ ዳር የተጣሉ በየጎርበት አገሮች እንዲሰደዱ የተደረጉ የቀድሞ የሕወሓት እና የብአዴን ካድሬዎችን ማሰባሰብ የጀመረው መጣፊያው ያጠረው በአጣብቂኝ የተወጠረው የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ እየመዘገበ በጥቅማ ጥቅም እየደለለ በመሰብሰብ ላይ ያለውን የቀድሞ ታጋዮች ሃይል በሰራዊቱ እና ደህንነት ውስጥ በፕሮፓጋንዳ እና መረጃ ሰራተኝነት በወሽመጥነት ለመድባቸው መሆኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::
የወያኔ ገበና አዋቂ ምንጮች እንዳሉት ከፖለቲካ ላቻ የጸዳ ጠንካራ እና በአቋሙ ጽኑ የሆነ የጋራ ሃይል ማጣቱ እንጂ ወያኔ ለመጣል በአሁን ወቅት የገባበት አጣብቂኝ ብቻ በቂ መሆኑን ሲገልጹ ለቀድሞ ታጋዮች ያደረገው ጥሪ በድርጅቱ ውስጥ ያለው የድል አጥቢያ አርበኞች ለሆዳቸው ብለው ከተጠጉ በኋላ በአደርባይነት ፖለቲካው ገደል ከተው ድርጅቱ ብውሸት እንዲሞላ እና ባለስልጣናቱ ከቀድሞ በባሰ መልኩ በተጋደደ ፖለቲካ እንዲመሩ መደረጉ ወያኔን የማይወጣበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተትው ተናግረዋል::በቻይና ተምረው የሕውሓትን ባለስልጣናት ይተካሉ የተባሉ ወጣቶች ግማሾቹ በእረፍት ሰበብ አውሮፓ ሂደው ሲከዱ የተቀሩት ደሞ ከአንጋፋ ታጋዮች ጋር አስተሳሰባቸው አለመጣጣሙ ሌላ አጣብቂኝ ፈጥሯል::እንዲሁም ሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን ዘረኝንት እና ዘረፋ የሰራዊቱን አባላት ወደ አስከፊ መተላለው እና መከዳዳት እየከተታቸው መሆኑን ታውቋል::በተጨማሪም በዋነኛነት በሕዝቡ ዘንድ ያልው ቅሬታ ማጉረምረም በተቃዋሚዎች አከባቢ ያለው ትግል የሰራዊቱን እና የደህነቱን አቋም በመፈታተኑ ድርጅቱ አደጋ ውስጥ ገብቷል::ብደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ አባላቱ በአላማ ሳይሆን በጥቅም ትሥሥር ስለተገነባቡ ድንገት የሚንዳቸው አደጋ ፊታቸው መደንቀሩን የድርጅቱ ምንጮች ጠቁመዋል::
እነዚህን እና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም የቀድሞ ታጋዮችን እያሰሰ እየተለማመጠ እየሰበሰበ ያለው ወያኔ በመውደቂያው ሰአት ታጋዮቹን ተገን ከለላ አድርጎ ስልጣኑን ልማስረዘም የተጠቀመበት ዘዴ የተበላበት እና ወንዝ የማያሻግር ስለሆነ በሰላም ስልጣኑን ለሕዝብ ቢያስረክብ ይሻለዋል ሲሉ ታዛቢዎች ያናገራሉ::ሕዝቡ የመጨረሻው ወቅት ላይ ነው ያለው የሚሉት ታዛቢዎች ግፍ ጽዋዋት ሞልታ እየፈሰሰች ስለሆነ እያንዳንዱ የወያኔ ባለስልጣን በሕዝብ ሃይል በፍትህ አደባባይ ቆሞ እንደሚቀጣ ሊያውቅ ይገባል ሲሉ ታዛቢዎቹ አክለው ተናግረዋል::
No comments:
Post a Comment