Monday, June 8, 2015

ርዕሳነ መምህራን መብታችን አልተከበረልንም አሉ


ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ርዕሳነ መምህራን በልዩ ልዩ ምክንያት ከቦታቸው ሲነሱ በአስተማሪነት የሚያገለግሉ ቢሆንም በዲግሪ ሲከፈላቸው የነበረው ደመዎዝ ተቀንሶ በዲፕሎማ ፣በሁለተኛ ዲግሪ የተመርቁ
ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሰሩ በመደረጋቸው እንዲሁም በራሳቸው ጥረትና ገንዘብ ዲግሪያቸውን የያዙ መምህራን በተመረቁበት የትምህር ዓይነት ማስተማር ባለመቻላቸው መምህራኑ ዲግሪያቸውን እንደተቀሙ እንደሚቆጥሩት ተናግረዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢ ርዕሳነ መምህራኑና መምህራኑ የተማርነው የትምህርት ዓይነት ባለመያዙ ጊዜያችን ባክኗል በማለት የሚናገሩ ሲሆን ለሌሎች የትምህርት እድል ሲሰጥ መከልከላቸውን በቅሬታ መልክ ያቀርባሉ፡፡
‹‹ አብዛኛው ርእሰ መምህራን ከደረጃቸው ዝቅ የሚሉበት አግባብ ፍትሃዊ አይደለም፡፡›› በማለት የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ በመጀመሪያው አመት አፈጻጸም ከፍተኛ በመሆን ተሸላሚ የነበሩ ርዕሳነ መምህራን ከየአካባቢው ካሉ
የትምህርት አመራሮች እና የፖለቲካ ሰዎች ጋር በስራ ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባትና የፖለቲካ አመለካከታቸ በቀጣዩ ዓመት ተገምግመው ዝቅተኛ አፈጻጸም አላቸው በማለት ከቦታቸው እንዲነሱ መደረጉ አሰራሩ በጥናት ላይ ያልተደገፈ
መሆኑን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡
‹‹ ችግሩ የተፈጠረው ከ2002 እሰከ 2004 ዓ.ም በተሰጡ ስልጠናዎች የሰለጠኑ የመጀመሪያ ደረጃ ርዕሰ መመህራን በዲፐሎማና ዲግሪ የትምህር ስራ አመራር ሲሰለጥኑ ተጨማሪ የትምህር ዓይነት በንዑስ ክፍል ባለመማራቸው ከቦታቸው
ሲነሱ ምድባቸውን ምን ይሆናል በሚል በተሟላ ሁኔታ ምላሽ የሚሰጥ ዝግጅት አለመደረጉ ነው፡፡ ›› የሚሉት የትምህርት ቢሮው ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ ተፈራ ፈይሳ፣ ትልቁን ክፍተት የፈጠረው የስልጠና ሞዳሊቲው ታስቦ አለመዘጋጀቱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በግላቸው ተምረው ዲግሪ የያዙ ከ1500 በላይ መምህራን በዲፕሎማ ደረጃ ቢያስተምሩም ወደ ሁለተኛ ደረጃ በመውሰድ ለመመደብ መቸገራቸውን ይናገራሉ፡፡ ርዕሳነ መምህራኑ ያለ አግባብ ከስራቸው መታገዳቸውን አስመልክተው ሲናገሩ
የሰው ሃይል አያያዛቸው ችግር እንዳለበት ጠቁመው፣አመራሩ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ከመምራት ይልቅ በዘፈቀደ የሚንቀሳቀስ አሰራር መኖሩ አግባብነቱ እንደማይታያቸው ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ተከታታይ አመታት ችግሩ ሳይፈታላቸው የቆዩ ርዕሳነ መመህራንና ዲግሪያቸው ሳይያዝላቸው የቆዩ መምህራን ችግሩ ሳይፈታላቸው በዚህ አመት ወደ ስራ መግባታቸው በመማር ማስተማሩ ሂደት ችግር እንዳለው የተናገሩት አቶ ተፈራ ቅሬታዎችን የምንፈታው በመንግስት ስለሆነ በየጊዜው እያጠናን ቅሬታ እንዳይኖር ማድረግ አለብን ፡፡ያለውን ቅሬታ በመቅረፍ ደረጃ መሰራት ያለበት ባለፉት ሶስት ዓመታት ቅንነት በሌላቸው አመራሮች በተከሰቱ ችግሮች ባለመፈጸማቸው ዋና
የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆን መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
አጎራባች ክልሎች የተከሰቱትን ተመሳሳይ ችግሮች ፈተው የመምህራን እና ርእሳነ መምህራንን መብት ያስከበሩ ሆኖ እያለ የአማራ ክልል ትምህር ቢሮ ችግሩን ለመፍታት ጥናት ላይ ነኝ በማለት አመታት ማስቆጠሩ እንዳስከፋቸው ቅሬታ
አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment