Saturday, August 1, 2015

የዓረና-መድረክ ኣባል የሆነውና ከዓመት በፊት "...ከዴምህት ጋር ግንኙነት ኣድርገሃል.." በሚል ክስት ለእስር የተዳረገው ወጣት ኣያሌው በየነ የ3ከ 6 ወር የእስር ቅጣት ተፈረደበት።

ወጣት ኣያሌው በየነ የሽረ ከተማ ኑዋሪ ሲሆን ታጣቂዎች ከቤቱ ኣስረው ወደ መቐለ ህቡእ እስር ቤት የነበረውና "ፔርሙዳ" ወይም ደግሞ "ጓንታንሞ" ተብሎ በተለምዶ የሚታወቀውና ሗላ የትግራይ ክልል ፖሊስ "ግዝያዊ የእስረኞች ማቆያ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ኣስቸጋሪ እስር ቤት ከ4 ወር በላይ ከታሰረ በሗላ ወደ መቐለ ወህኒ ቤት ተወሰዶ ነበር።

ከዛም ወደ ኣክሱም እስር ቤት ከተዘዋወረ በሗላ ሓምሌ15 / 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት የ3 ዓመት ከ6 ወር የእስር ቅጣት ተፈርዶ በታል።

ኣያለው በየነ በጥንካሬውና በጀግንነቱ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱ የዓረና ኣባላት የሚጠቀስ ሲሆን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች፣ ፖሊሶችና የድህንነት ሰዎች በተደጋጋሚ የማባበል፣ የማስፈራራት፣ የድብደባ፣ የእስራት ኣደጋዎች ተጥለውበታል።

በተለይ በ2002 ዓም ምርጫ ተከትሎ በተወለደበት ውቕሮማራይ ከተማ የሚገኘው ቤቱ በራፍ ፈንጅ ኣጥምደውበትና ወደ ቤቱ ፈንጅ ወርውሮውበት ከክፉ ለጥቂት የተረፈ ቆራጥ የዓረና-መድረክ ኣባል ነው።

በሚኖርብት ሸረ ከተማም የድህንነት ሃይሎች ሌሊት ከቤቱ ኣፍነው በመውሰድ በበረሃ ቀጥቅጠው ጥለውት ሂወቱ በተኣምር ተርፋለች።

ይህ ወጣት እስከ ሂወቱ ሊያጣበት የሚችል ኣደጋዎች በገዢው ፓርቲ ቢደርሱበትም ካመነበት የሰለማዊ መንገድ ሳይለቅ እየታገለ ሳለ "ከዴምሕት ግንኙነት ኣለህ" ተብሎ ተከሶ ኣሰቃቂ ድብደባዎችና ቶርቸሮች ደርሶበታል።
የፍርድ ሂደቱም ምንም ማስረጃ ባይገኝለትም ለ3 ከ6 ወር እስር ተዳርጎ ይገኛል።

የዓረና-መድረክ ኣባላት ለመግለፅ የሚዳግቱ ግፎች እየተፈፀመባቸውም ቢሆን ካመኑበት ኣላማ ንቅንቅ የሚሉ ኣልሆኑም። ወጣት ኣያሌው በየነም በያዘው ፖለቲካዊ ኣቋም ምክንያት ለእስር ተዳርጎ ይገኛል።

ህወሓት የህሊና እስረኞች ትፍታልን። የፖለቲካ ልዩነት እንደ ወንጀል ወስዳ ማንገላታት፣ ማስፈራራት፣ መደብደብ፣ ማሰርና መግደል ታቁም።

ነፃነታችን በእጃችን ነው...!

IT IS SO....!

No comments:

Post a Comment