Saturday, December 12, 2015

ኢትዮጵያውያን በቺካጎ በወያኔ የተጠራውን ስብሰባ ሳይካሄድ በሕብረት በተኑት | ሐተታ ከቪዲዮ ጋር




girma biruu
(ዘ-ሐበሻ) በቺካጎ የወያኔ ”የስለላ አምባሳደር እና የደህንነት ሰራተኛ” ሆኖ እንዲያገለግል የታጨውን አቶ በፍቃዱ ረታ ለመሾም በቺካጎ ትሩማን ኮሌጅ ውስጥ የነበረው ስብሰባ የኢትዮጵያ ትውልድ ባላቸው ዜጎች መበተኑ ተሰማ::
ለዚህ የአምባሳደርነትት ሽልማት የመጡት በዲሲ የሚገኙት የወያኔ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ ሲሆኑ አንድም ንግግር ሳያደርጉ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ድርቅ እና በተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን አስከፊ ግድያ እስካልቆመ እና የሚላላኩለት መንግስታቸው ከስልጣን እስካልወረደ ድረስ ማንም ሰው አምባሳደርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የማይወክሉበትን ኢትዮጵያዊነት ሊያሳዩ አይችሉም በማለት ስብሰባው እንዲበተን አድርገዋል::
አቶ በፍቃዱ እረታ በቅጽል ስማቸው (ስልሳ ጎራሽ) እየተባሉ የሚጠሩት እኝህ ግለሰብ በችካጎ ከተማ የወረዳ 46 የአልደርማንነት ተወዳዳሪ ለመሆን ሲጥሩ የነበረ ሲሆን ሳይሳካላቸው በዝረራ የወደቁ እና ከዚያም በሁዋላ በወያኔ መደብ ላይ የልጥቀምህ ጥቀመኝ ስራ የሚሰሩ አገልጋይ መሆናቸውን ከቺካጎ የኦሮሞ ማህበረሰብ ደረሰን ዘገባ ያመለክታል::
ይህን አይነት የተቃውሞ ሰልፍ በወያኔ መንግስት ላይ በችካጎና አካባቢዋ ሲደረግ የመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ህብረተሰቡ ወያኔ የሚያደርገውን የቺካጎ ስብሰባ በአጽንኦ ከመመልከታቸውም በላይ አንድም ነገር የማያደርጉ ዜጎች የነበሩ ሲሆን በአሁን ሰአት በሃገሪቱ ላይ እየደረሰ ያለው አስከፊ አገዛዝ ግን ቁጣቸውን ሊቀሰቅሳቸው እንደቻለ የዚህ የተቃውሞ ሰልፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ገልጾአል።
አቶ በፍቃዱ ረታ ለአልደርማንነት በ2011 በችካጎ እና አካባቢዋ የተወዳደሩ ሲሆን ከዚያም በፊት የወያኔ መንግስት የገለልተኛ የምርጫ አጣሪ ኮሚቴ ብሎ ጠርቷቸው; በአዲስ አበባ በመሄድ; “የወያኔ መንግስት ፍትሃዊ እና የተሳካ ምርጫ አድርጓል በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የተገደለ ዜጋ የለም” ብለው የሸመጠጡ ሰው ናቸው ተብሎ ይነገርላቸዋል::


#OromoProtests Oromos in Chicago disrupt Girma Birru's meeting in Chicago
Posted by Jawar Mohammed on Saturday, December 12, 2015

No comments:

Post a Comment