ሐምሌ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው አክሽን ኤይድ በካናዳ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት ይሽከረከራሉ ያላቸውን 77 ሀገሮችን የአዲስ አበባው ጉባዔ አላማ እንዳይሳካ እንቅፋት እየፈጠሩ ነው ሲል ተቃውሞ አቅርቧል።
የድርጅቱ ኃላፊ አዲያምኖ ካምፖሊና የበለጸጉት ሀገሮች ጥቂት ሀብታም ሀገሮች የበለጠ ሀብታም ፤ብዙሀኑ ደሀ ሀገሮች ደግሞ ይበልጥ እንዲደኸዩ እየሠሩ ነው ሲሉም ከሰዋል።
አሁንም በዚህ ጉባዔ ላይ የበለጸጉት ሀገራት ይዘው ይቀረቡት እቅድ ሀብታሞች ይበልጥ የሚያበለጽግና ድሀዎችን ይባስ ድህነት ውስጥ የሚከት ነው ያሉት ካምፖሊና፤ ይህ እንዲሆንም ካላቸው ፍላጎት በመነሳት በዚህ ጉባኤ ላይ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተስማምቶ አንድ ውሳኔ ላይ እንዳይደርስ አላስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን እየደረደሩ ነው ብለዋል።

No comments:
Post a Comment