Friday, July 3, 2015

መንግስት በተለያዩ የሙያ ትምህርቶች አሰለጥናችሁዋላሁ በማለት የወሰዳቸው ተማሪዎች አብዛኞቹ ተበተኑ


ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ አመት በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ አሰማራችሁዋለሁ በሚል መንግስት ካሰበሰባቸው ከ2 ሺ 500 ያላነሱ ወጣቶች 1 ሺ 500 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው በተለያዩ የመከላከያ ተቋማት ቢመደቡም፣ ቃል የተገባላቸው እና በተግባር የሚያዩት ነገር ባለመጣጣሙ ስራቸውን ጥለው መጥፋታቸውን ሰልጣኖች ተናግረዋል።
አሚባራ በሚባለው አካባቢ የሚገኝ ጫካ መንጥረው ህንጻ በመስራት ስልጠና የጀመሩ ወጣቶች እንደሚሉት፣ መንግስት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ እንደሚያሰማራን ቃል ቢገባላቸውም፣ በስልጠናው ይህ ነው የሚባል ነገር አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ሁሉም ተማሪዎች ወደ መጡበት አገር ለመመለስ በእግራቸው እስከ አዋሽ አርባ መሄዳቸውን የሚናገሩት ሰልጣኞች፣ የመንግስት ባለስልጣናት ችግሩን እንደሚፈቱላቸው በመግለጻቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
የለብ ለብ ስልጠና እንድንወስድ ከተደረገ በሁዋላ በተለያዩ ወታደራዊ ተቋማት ውስጥ መመደባቸውን የሚናገሩት ሰልጣኖች፣ 4 ሺ ብር ይከፈልችሁዋላ ተብሎ ቃል ቢገባልንም በወር የሚሰጠን 800 ብር ብቻ ነበር ይላሉ። በዚህም የተነሳ አብዛኛው ሰልጣኝ ጠፍቶ ወደ አገሩ መመለሱን ተናግረዋል

1 comment:

  1. Government should utilize the chance to have million dollar buildings with only 200 dollar per month.

    ReplyDelete