Thursday, July 30, 2015

የእስር ዜና የቀድም የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው አቶ መኮንንት ብርሃኑ ታሰረ።


የቀድም የአንድነት ለዲምክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት አባል የነበረው የወረዳ 28 አባል የአዲሰ አበባ ምክርቤት አባልና የየካ ክፍለከተማ አሰተባባሪ ኮሚቴ አበል የነበረው አቶ መኮንንት ብርሃኑ ታሰረ።
ባለፈው ሰኞ ከጠዋቱ በ4:00 ሰአት የመኖሪያ ቤቱ የጦር መሳሪያ በታጠቁ ሰዋች ተከቦ ቤቱ ከተበረበረ በሆላ እሱን በቁጥጥር ስር አውለው ወደአልታወቀ ቦታ እንደወሰዱት ከታወቀ ግዜ ጀምሮ ያለበትን ቦታ ለማወቅ ትልቅ ጥረት ሲደረግ ቆይቶል።
አቶ መኮንንት ብርሃኑ በአሁኑ ሰአት በመአከላዊ እስርቤት እንደሚገኙ በተደረገው ብርቱ ጥረት የታወቀ ሲሆን ከመንም ጋር እንዲገናኙ አልተፈቀደም።
አቶ መኮንንት ብርሃኑ የቤተሰብ ሃላፊ ባለትዳር የልጆች አባት ነው። ለረጅም አመታት በትግል ውስጥ የቆየው የአንድነትም መስራች አባል ሲሆን ፓርቲው በህገወጥ መንገድ ከመፍረሱ በፊት የምርጫ 2007 አሰተባባሪ ኮሚቴ ውስጥና በፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ኮሚቴ የደቡብ ጎንደር አደራጅ ኮሚቴ ውስጥ የሰራ ጠንካራ አባል ሲሆን የፀጥታ ሃይሎች ጥብቅ ክትትል ይደረግበት እንደነበር ወደሃገሩ ዘመድ ጥየቃ ሲሄድም ሲመለስም ከፍተኛ ክትትል እንዳለበት ሲገል የቆየ ከመሆኑም በላይ በቅርቡም ከዘመዶቹ ጋር በደብረታቦር መቆየት ባለመቻሉ ተመልሶ የመጣ ሲሆን ጫናው እንደበዛ ለጋደኞቹና ለቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ መናገሩን ይገልፃሉ በመጨረሻም በሃይል በቁጥጥር ሰር ውሎ በመአከላዊ እስር ቤት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎል።

posted by Aseged Tamene

No comments:

Post a Comment