Thursday, July 30, 2015

ከአዲስ አበባ ከተማ በደህንነት ኃይሎች የታፈኑት ሃያዎቹ ሙስሊሞች ዛሬ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው ድጋሚ ለሐምሌ 28 ቀጠሮ ተሰጣቸው ።


በከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ወጣት ወንድሞቻችን እና አንድ እህታችን፣ የቢላል ራዲዩ ጋዜጤኞች ካሊድ ሙሃመድና ዳርሶማ ሶሪን እንዲሁም በሐሰት አልመሰክርም በማለቱ ብቻ በእስር ላይ የሚገኘው ወንድም ሙጂብ አሚኖን ጨምሮ በአጠቃላይ 20 የሚሆኑ ሙስሊሞች ከ 5 ወር በፊት በደህንነት ኃይሎች ታፍነው በቅርቡ ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዘዋወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው ።

እነዚህ ሙስሊሞች በቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ ጠዋት ላይ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ያለምንም ምክንያት ቀጠሮ መስጠት የማይሰለቸው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ለሐምሌ 28/2007 ቀጠሮ ሰጥቷቸዋል ።

ፍትህ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!

Aseged Tamene

No comments:

Post a Comment