Tuesday, July 28, 2015

በጋሞጎፋ ዞን ከብሄር ግጭት ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ሰዎች ታሰሩ


ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወኪላችን እንደገለጸው ከሁለት ሳምንት በፊት በአርባምንጭ ከተማ ሊደረግ የታቀደው የተቃውሞ ሰልፍ በገዢው ሃይል የጸጥታ አባላት እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ፣ ከ120 በላይ ሰዎች ተይዘው በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረዋል።
አንድ የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነ ሰው የጋሞን ብሄረሰብ ታሪክ አንቋሾ መጽሄት አሳትሟል በሚል የተጀመረው ተቃውሞ እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ፣ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞ ሊያሰሙ ይችላሉ የሚሉዋቸውን እዬያዙ በማሰር ላይ ናቸው። መጽሄቱ መታተሙን ተከትሎ የአካባቢው ባለስልጣናት ከሁለት የተከፈሉ ሲሆን፣ አንደኛው ወገን፣ መጽሄቱን በማሳተም በኩል ድጋፍ የሰጡ ባለስልጣናት በህግ ይጠየቁ የሚል አቋም ይዟል።
ሰሞኑን ከታሰሩት መካከል የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ የአካባቢው ሽማግሌዎች ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment