Monday, April 13, 2015

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የርሃብ አድማ መቱ

ነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የርሃብ አድማ መቱ በማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድና ፍቅረ ማሪያም አስማማው አብራቸው በታሰረችው እየሩስ ተስፋው ላይእየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትበመቃወም የርሃብ አድማ መቱ፡፡ ብርሃኑና ፍቅረማሪያም ከትናንት የትንሳኤ በዓል ጀምረውየእርሃብ አድማ ያደረጉ ሲሆን በትናንትናው ዕለትየገባላቸውን ምግብ እንዳልበሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡እየሩሳለም ተስፋው ከሳምንት በላይ ብቻውን እንድትታሰር ተደርጋ ከፍተኛ ምርመራእየተደረገባት ሲሆን ከቤተሰቦቿ ጋር እንዳትገናኝ ተደርጋለች፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ጥበቃ ፖሊሶችቤተሰቦቿ ስለ እየሩስ በሚጠይቁበት ወቅት ‹‹መግባት አይቻለም›› ከማለት ውጭ ምክንያቱን እንደማይናገሩም ከቤተሰቦቿ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡እነ ብርሃኑ እየሩስ ተስፋው ላይ እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እስካልቆመ ድረስ የርሃብ እድማቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡


Source:  Emebet Girma

No comments:

Post a Comment