Saturday, September 24, 2016

ዓለም አቀፍ ደረጃ October 3, 2016 በጀርመን ኢምባሲ ደጃፍና እዚያው ጀርመን በርሊን October 2, 2016 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

ዓለም አቀፍ ደረጃ October 3, 2016 በጀርመን ኢምባሲ ደጃፍና እዚያው ጀርመን በርሊን October 2, 2016 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ



google
ዓለም አቀፍ ደረጃ October 3 2016 በጀርመን ኢምባሲ ደጃፍና እዚያው ጀርመን በርሊን October 2 2016 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ
ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን
ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ።
October 2 2016 በርሊን
የጀርመን መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ወደ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ጉዞ አጋጣሚ በማስመልከት
እሁድ ጠዋት 10:00 October 2 . 2016
አድራሻ Willy-Brandt-Str. 1 · 10557 Berlin
የጀርመን መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ጽ፨ቤት ፊትለፊት ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን
በኢትዮጵያ በንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየትካሄደ ያለው አፈና እና ጭፍጨፋ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የለጋሽ አገር መሪ ጉዞ የመጀመሪያ ነው። ለታፈኑት ለሚታፈኑት ለተገደሉት ለሚገደሉት ለታሰሩት ለሚታሰሩት ለተፈናቀሉት ለሚፈናቀሉት ለተጨፈጨፉት ለሚጨፈጨፉት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ኑ በበርሊን ድምጻችንን እናሰማ።
የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።
በዚህ አጋጣሚ በአለም ያሉ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰኞ በኦክቶበር ሦስት Monday October 3. 2016 ጀርመን የተዋሃደችበት የጀርመን መንግስት በጀርመን የምስራቁን ከዲክታተር ወደ ነጻነት ዲሞክራሲ በሚያከብርበት ቀን በኢትዮጵያ የጀርመን መንግስት እየደገፈው ያለውን የሰብአዊ መብት ረጋጭ ስርዓት በአለም ለማጋለጥ የፈሰሰውን እና የሚፈሰውን የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም በማስታወስ በአለም ላይ በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ እንድትጠሩ እንድታደርጉ ዘንድ በማክበር እንጠይቃለን። በኢትዮጵያ በንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየትካሄደ ያለው አፈና እና ጭፍጨፋ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የለጋሽ አገር መሪ ጉዞ የመጀመሪያ ነው።
ለመረጃ ያህል
የጀርመን መንግስት እና ህዝብ እ.ኤ.አ ኦክቶበር ሦስት የምስራቁም ጀርመን ክፍል ከዲክታተር ተላቆ የህግ የባላይነት ዲሞክራሲ እንዲሁም ሰብአዊ መብቶች በማረጋገጥ ጀርመን የተዋሃደችበት ቀን ሆኖ በዲክታተር የተሰቃዩት እሚታወሱበት ዲክታተር የሚወገዝበት ቀን ነው።
በተለይ የጀርመኑ ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ እንዲሁም መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ሁለቱ ጀርመኖች እስከ ተዋሃዱበት ድረስ በዲክታተር አገዛዝ ስር በምስራቅ ጀርመን ዜጋ እና ነዋሪ ነበሩ ሁለቱም ነጻነት ያገኙት ሁለቱ ጀርመኞች ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው ሁለቱም በዲክታተር ስርታአት የማይቻለውን በዴሞክራሲ ሁለቱም የተዋሃደው ጀርመን የአገር መሪ ለመሆን በቅተዋል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።
ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ በ እ.ኤ.አ March 17 – 20፣ 2013 የኢትዮጵያ ጉዞዋቸው ከፖለቲከኞች እና የታወቁ ሰዎች ተገናኝተው ይህ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ የድሮ አገሬን ምስራቅ ጀርመንን ያስታውሰኛል ብለው ነበር። በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን ጥያቄ በእዚሁ በጀርመን ኤምባሲ በተካሄደው (ሪሴፕሽን) አቀባበል ላይ ተጋብዘው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን በጹሁፍ የገለጡት ነው ። ዶር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል የጹሁፍን ኮፒ ልከውለታል ደርሶታል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።
ጂ.አይ.ዜድ ወይም በቀድሞ ስሙ ጂ ቲ ዜድ በተባለው የጀርመን የርዳታ ሚኒስትር ስር የሚተዳደር ድርጅትም ባለፈው አመት 2015 የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ላይ ሦስት ሺ ወጣቶች የጀርመንን ሰንደቅአላማ ቀለም በማስለበስ የጀርመንን ውህደት ምስራቅ ጀርመን ከዲክታተር ሥርዐት ተላቅቃ ወደ ሰብሳአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲሁም የህግ የበላይነት ከተረጋገጠበት ምዕራብ ጀርመን ጋር የ ሃያ አምስተኛ አመት መዋሃድ በአዲስ አበባ አስከብሯል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።
ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ
ጀርመን

No comments:

Post a Comment