Wednesday, November 4, 2015

በጅጅጋ የንግድ ቤቶች ተቃጠሉ



ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታይዋን በሚባለው አካባቢ ይሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች፣ ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ እሳት ድርጅታቸው እስከ ሙሉ ንብረታቸው እንደወደመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ድርጊቱ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ መንግስት በአካባቢው ለሚያሰራው መንገድ ድርጅቶችን በማቃጠል ካሳ እንዳይከፍል ለማድረግ ነው በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በቃጠሎው ከ15 በላይ የንግድ ድርጅቶች የወደሙ ሲሆን፣ ፖሊሶች ህዝቡ እሳቱን እንዳያጠፋ ሲከላከሉ ታይቷል። ይህም ሆን ተብሎ የተቀነባበረና ነጋዴው ለሚፈርስበት ድርጀቱ ካሳ እንዳያገኝ ተብሎ የተደረገ ነው በማለት ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment