Wednesday, November 4, 2015

የአቶ ፋንታሁን ልጅና አንድ የሰማያዊ የምክር ቤት አባል በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ


ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት መግባባትና መተባበር ሊቀመንበር የሆኑት የአቶ ፈንታሁን ብርሃኑ የ13 አመት ሴት ልጅ በአንድ ወጣት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል፣ ሌላው የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ አበራ ሃይለማርያምም በዚሁ ወጣት ተገድለዋል። አቶ ፋንታሁን ለኢሳት እንደተናገሩት ጎረቤታቸው የሆኑት አቶ አበራ የተገደሉት ምናልባትም ጩኸት ሰምተው ልጃቸውን ለመታደግ በመሞከራቸው ሳይሆን አይቀርም። ወጣቱ ግድያውን የፈጸመው ትናንት ምሳ ሰአት ላይ ሲሆን ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ በእሳት ለማቃጠል ሲሞክር ጎረቤቶች ጭስ አይተው ሲሯሯጡ ገዳይን ለመያዝ ችለዋል። አቶ ፋንታሁን ሰሞኑን ተከታታይ ማስፈራሪያ በስልክ ሲደርሳቸው ቆይቷል። ለእኔ የታሰበው ለልጃው መትረፉን አቶ ፋንታሁን ገልጸዋል።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ለቀብር እጅግ በርካታ ህዝብ የተገኘ ሲሆን፣ ተቃውሞ ያሰሙት ወጣቶች ከፖሊስ ጋር መጠነኛ ግጭት ፈጥረው ነበር። አቶ ፋንታሁን ከዚህ ደም ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውለብለብና የማህበሩን አላማ ሲያስተዋውቁ ተይዘው ታስረው ነበር።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment