Monday, November 30, 2015

Oromo Students Protest storified




The Master Plan that sparked a wide protest can be found here
https://t.co/0LHMRr1kAI #OromoProtests #Ethiopia pic.twitter.com/LqwCBmGoEp






















































































About 30 Oromo students were injured at Haromaya University when federal police and Agazi were attacked them in their dormitory.


About 30 Oromo students were injured at Haromaya University when federal police and Agazi were attacked them in their dormitory.


Source : http://www.bilisummaa.com/about-30-oromo-students-were-injured-at-haromaya-university-when-federal-police-and-agazi-were-attacked-them-in-their-dormitory/

Thursday, November 26, 2015

Police: Two Million Ethiopians Violating Residence Conditions

Khartoum - A High level police official disclosed the number of foreigners residing in violation of the law in Khartoum state, has reached three million. Two million are from the state of Ethiopia and 200,000 from Eritrea, foreigners from other nationalities residing illegally in Sudan has totaled 52650.
Khartoum State Governor Lt. Gen. Abdulrahim Mohamed Hussein said this on Tuesday, whilst addressing the conference of the issues affecting the security and criminal status in Khartoum, organised by the state police on recommendations by the security committee. He announced issues related to foreign presence and human trafficking, are of deep concern to the government.

Source : http://news.sudanvisiondaily.com/details.html?rsnpid=257324

Tuesday, November 24, 2015

በቴፒ ከተማ ውጥረት ነግሷል

በደቡብ ምዕራብ ቴፒ ከተማ የተቀሰቀሰውን አስተዳደራዊ አለመግባባት ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው መስፈሩ ተገለጠ።

በከተማዋ ላይ የተነሳው የይገባኛል አስተዳደራዊ ጥያቄ ስምምነት ባለማግኘቱ በርካታ ሰዎች በተቃውሞ ጫካ መግባታቸውንና ድርጊቱ በከተማዋ ውጥረት ማንገሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከሚዛን ተፈሪ ወደ ቴፒ፣ ከሸሸንዳ ከተማ ወደ ቴፒ፣ ከሚሻ ከተማ ወደቴፒ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ በፌዴራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥጥር እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ታውቋል።

በንግድ እንቅስቃሴዋ የምትታወቀው የቴፒ ከተማም ከወትሮ በተለየ መልኩ የስጋት ቀጠና ሆና መሰንበቷን የተከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በይፋ የተገለጸ የሰዓት እላፊ ገደብ ባይኖርም የከተማዋ ነዋሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይፈቀድላቸው ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

ቴፒ ከተማ የምትገኝበት የኪ ወረዳን ለማስተዳደር በሸኮ ብሄረሰብ ተወላጆችና በሸካ ብሄረሰብ ተወላጆች መካከል ፖለቲካዊ ጥያቄ መነሳቱንና ችግሩ እልባት አለማግኘቱን የከተማዋ አስተዳደር ይገልጻል።

አስተዳደራዊ ጥያቄው መግባባትን ሊፈጥር ባለመቻሉም ተቃውሞ ያስነሱ በርካታ ሰዎች ጫካ ገብተው ኣንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን፣ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እነዚህን ሃይሎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ ከፍቶ እንደሚገኝ ታውቋል።

ይሁንና ድርጊቱ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የተፈጠረው ችግር ፖለቲካዊ መፍትሄን እንደሚፈልግ የገለጹት ነዋሪዎች፣ የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ በተጠሩ መድረኮች አስተያየት የሰጡ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስረድተዋል።

“በአደባባይ ሃሳብን መግለፅ በራስ እንደመፍረድ ይቆጠራል” ሲሉ ነዋሪዎቹ የችግሩን አሳሳቢነት ገልፀዋል። ከአመታት በፊት ጀምሮ በከተማዋ የአስተዳደራዊ ጥያቄዎች ሲነሱ መቆየታቸው ይታወሳል።

ባለፈው አመት የቴፒ ወህኒ ቤትን የሰበሩ ታጣቂዎች የፖሊስ አዛዡን ጨምሮ አራት ፖሊሶች በመግደል እስረኞቹን ይዘው ወደጫካ መግባታቸው ይታወሳል። የመንግስት ሃይሎች ከእነዚህ ታጣቂዎች ጋር ለመደራደር ያደረጉት ሙከራ በድምፅ ተቀርጾ ለኢሳት መድረሱንና ይህም መዘገቡ አይዘነጋም።

Source:: Ethsat

የመንግስት ደህንነቶች የኢሳትን ዌብሳይት ሰብረው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ


ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመረጃ ደህንነት ባለሙያዎች በማስረጃ አስደግፈው እንደገለጹት የኢህአዴግ የመረጃ ደህንነት ሰራተኞች መብራቱ በሚል ስም ኢሳት በኢንተርኔት የሚያሰራጨውን ዌብሳይት ሰብረው በመግባት፣ ጉዳት ለማድረስ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
የኮምፒዩት መለያ ቁጥሩ 197. 156. 86. 162 የሆነ አዲስ አበባ የሚገኝ ኮምፒዩተር መብራቱ በሚል የመግቢያ ስም ወደ ወደ ኢሳት ዌብሳይት ለመግባት ቢሞክርም አልተሳካለትም።
መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት የስለላ ሶፍትዌሮችን ለመጠቀም ሲሞክር መጋለጡ የአለም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የኢሳትን የቴሌቪዥን ስርጭት ለማፈን ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርጓል። ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በሁዋላ አሁን ደግሞ ተመሳሳይ ስም በመጠቀም የኢሳትን ዌብሳይት ሰብሮ መረጃዎችን ለመጥፋት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ ገዢው ፓርቲ ከኢሳት ጋር የገጠመውን ትንቅንቅ የሚያሳይ ነው።

Source:: Ethsat

ዜጎች እርዳታ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ቢሆንም እስካሁን በቂ ምላሽ ሊሰጣቸው አልቻለም


ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ ክልሎች ለኢሳት የሚላኩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እርዳታ የሚጠይቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ በቂ የሆነ እርዳታ እየተከፋፈለ አይደለም።
በአማራ፣ በትግራይ ፣ በሶማሊ፣ በደቡብና በአፋር የእለት ደራሽ ምግብ የሚጠይቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ህጻናት በአልሚ ምግብ እጥረት የተነሳ ለበሽታ እየተዳረጉ በመሞት ላይ ናቸው፡፡የረሃቡ ሁኔታ አስከፊ እየሆነ ቢመጣም በመንግስት ባለስልጣናት በኩል የሚሰጠው መግለጫ እርስ በርስ የሚጣረስ በመሆኑ፣ በተረጅዎች ህይወት ላይ ተጽኖ እያሳረፈ ነው።
በአማራ ክልል 69 ወረዳዎች በድርቅ የተጠቁ ሲሆን፣ ባለፈው መስከረም ወር በተደረገ ጥናት 1 ሚሊዮን 400 ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚሹ ቢገልጽም፣ ይህ አሀዝ በመጪው ወር ይፋ በሚደረው ጥናት ላይ በእጥፍ ጨምሮ እንደሚገለጽ መረጃዎች ያመለክታሉ። የክልል አደጋ መከላከል ዝግጁነት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ሽለስ ተመስገን በአንዳንድ አካባቢዎች በክረምቱ ወራት ለ2 ቀን ብቻ ዝናብ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ወትሮ ዝናብ እጥረት አጋጥሟቸው የማያውቁት ወረዳዎች እንኳ የዝናብ እጥረት ያጋጠማቸው መሆኑን ባለስልጣኑ አልሸሸጉም። የዋግ ህምራ ሁሉም ወረዳዎች ፤ የሰሜን ጎንደር ምስራቃዊ ክፍል- በለሳ ፣ ጠለምት ፣ወገራ ፣ ጃን አሞራ ፣ የደቡብ ወሎ ሁሉም ወረዳዎች- መቅደላ ፣ አርጎባ ፣ ከላላ ፣ ከዚህ በፊት ተርበው የማያውቁት የምስራቅ ጎጃም የአባይ አዋሳኝ ስምንት ወረዳዎች በአጠቃላይ 800 ቀበሌዎች በርሃብ ውስጥ እንደሆኑ የክልሉ የአደጋ መከላከል ጽ/ቤት ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡
በዋግ ህምራ ስሃላ ወረዳ በአመት ውስጥ ሁለት ቀናት ብቻ ነው ዝናብ ያገኘው። ሰቆጣ ፤ አበርገሌ ፤ ደሃና በከፋ ሁኔታ በድርቅ ተጠቅተዋል። በሰሜን ወሎ፣ የራያ ሰፊ መሬት ዝናብ ካዬ በመክረሙ ከፍተኛ አደጋ ተደቅኖበታል። በክልሉ በድርቅ ከተጎዱት 69 ወረዳዎች መካካል 35 ቱ በከፋ ሁኔታ ላይ ሲገኙ 34ቱ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠቅተዋል። በሁለተኛ ደረጃ ተጠቂ የተባሉት ለሶስት ወራት የሚያቆይ የእህል ክምችት ያላቸው ናቸው፡፡
በአሁኑ ስዓት መንግስት ለአንድ ሰው 15 ኪሎ ግራም ስንዴ ወይም በቆሎ ለወር ደግሞ ግማሽ ሌትር ዘይት እያደለ መሆኑን ባለስልጣኑ ተናግረዋል።
በአሁኑ ስዓት ቀዳሚው ችግር የመጠጥ ውሃ እጥረት ነው ያሉት ኃላፊው፣ በምግብ እና የጤና ችግርም በውሃ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የንፅህና እና የውሃ ወለድ በሽታዎች ተከስተዋል ብለዋል፡፡
በአልሚ ምግብ እጥረት የተጎዱ እናቶች እና ህፃናት አሉ ያሉት ባለስልጣኑ ፣ ህፃናት በአልሚ ምግብ ችግር መሞታቸውንም ይፋ አድርገዋል በትግራይ ደግሞ ከ52 ወረዳዎች 36ቱ በድርቅ ተመተዋል። በክልሉ የሚሰጠው እርዳታ ከፖለቲካ ጋር መያያዙንም ተረጅዎች እየገለጹ ነው። የመንግስት እዳ እና የወይን ጋዜጣ ያልከፈሉ ሰዎች እርዳታ እንደማያገኙ እንደተገለጸላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ ቦሲያ፣ አጋምዜና ሌሎችም ቀበሌዎች የተረጅውን ቁጥር ለማጥናት ለተላኩ ባለስልጣናት በሚል እያንዳንዱ ተረጅ በነፍስ ወከፍ 10 ብር እንዲያዋጣ ተገዶ፣ አጥኚዎች በግና ፍየል ታርዶላቸው ሲመገቡ መሰንበታቸውና ተረጅዎች ” ብዙዎቻችንን ሳይመዘግቡን ሄዱ” በሚል መበሳጨታቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ገልጸዋል። ጥናቱን ለማካሄድ የተላኩት ከግብርና አቶ አስችሌ አሰፋ፣ ከከምግብ ዋስትና ወ/ሮ አስካለማርያም ተገኘ ፣ ከብአዴን የድርጅት ጉዳይ አቶ ሰጠኝ ንጉሴ እና ሁለት ሌሎች ተወካዮች ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳምንታዊ ዘገባ ባወጣው መረጃ ደግሞ ድርቁ ከፈጠረው ቻና በተጨማሪ፣ 210 ሺ 600 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ብሎአል።መንግስት የእርዳታ እህል በቅርቡ ስራ የጀመረውን ባቡር በመጠቀም ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ለማመላለስ ማቀዱን ገልጿል።

Source:: Ethsat