Tuesday, September 8, 2015

በሶማሊያ የእስርስበርስ ግጭት እንዲፈጠር የኢትዮጵያ ጦር ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ


ጷግሜን ፫ (በሶማሊያ የእስርስበርስ ግጭት እንዲፈጠር የኢትዮጵያ ጦር ምክንያት እየሆነ ነው ተባለሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኞ ዕለት በሶማሊያ ጌዶ ግዛት የቀድሞ አስተዳዳሪ የነበሩት ሞሃመድ አብዲ ከሊል ከባድ መሳሪያ ከታጠቁ አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን ጋርባሃሬ ከተማ ሲገቡ አካባቢው የጦርነት ድባብ ውስጥ መውደቁን የከተማዋ ነዋሪዎች እማኝነታቸውን ሰጡ።
የገርባሃሬ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚደገፈው አዲሱ የጁባላንድ አስተዳዳሪ አህመድ ማዶቤ በከተማዋ በኃላፊነት መሾሙ እየታወቀ የሞሃመድ ከሊል ወደ ከተማዋ ተመልሶ መምጣት እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።
የቀድሞ አስተዳዳሪ የነበሩት ሞሃመድ አብዲ ከሊል ደጋፊዎችና የከተማው አዲስ ነዋሪዎች አዲሱን አስተዳደር እና የኢትዮጵያን ሰራዊቶች በመንቀፍ በከተማዋ ገርባሃሬ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።
በተቆጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ግፊትና ተቃውሞ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ከሞሃመድ አብዲ ከሊል መኖሪያ አካባቢ ተባረዋል።ቢሆንም ግን የኢትዮጵያ ወታደሮች አካባቢውን ለብዙ ሰዓታት ከበው የቆዩ ቢሆንም ንጋት ላይ ስፍራውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል።
የጁባላንድ አስተዳደርና የኢትዮጵያ ሰራዊት ግን የከሊል የግል ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ መግባታቸውን አስተባብለዋል ሲል ማረግ ዘግቧል።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment