Thursday, August 20, 2015

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብቻ በያመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ይዘረፋል ተባለ


ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመንን አስመልክቶ በ51 የአዲስ አበባ አድባራት ባካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት፣ በየወሩ 100 ሚሊዮን ብር፣ በዓመት ደግሞ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በሙስና እንደሚዘረፍ ገልጿል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት ይዞታ ቢኖሯትም የሚገባውን ያኽል ተጠቃሚ እንዳልሆነች ሰሞኑን ለጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ የቀረበው የአዲስ አበባ አድባራት የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመን ጥናታዊ ሪፖርት ማረጋገጡን ፓትርያርኩ ጠቅሰዋል፡፡
ከቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ባሕርይ ጋር የማይስማሙ የሙስና እና የሥነ ምግባር ብልሹነትን ለማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ “ጭላንጭል እየታየበት ነው” ያሉት ፓትርያርኩ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልዕልና እና ሕይወት እስኪመለስ በሰላማዊ መንገድ እና በአቋም መታገላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳስበው በቀጣዩ ዓመት 2008 ዓ. ም. ቤተክርስቲያኗ ከሙስና የፀዳ አስተዳደር ይኖራታል ማለታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment