Thursday, August 20, 2015

በሰቆጣ ከተማና አካባቢዋ ከወር በሁዋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ዝናብ በመዝነቡ ህዝቡ ደስታውን ገለጸ


ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ሰኔ 15 እና 16 የክረምቱ ዝናብ ከዘነበ በሁዋላ፣ ዝናብ ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት አልዘነበም። ሃምሌ 29 ቀን ደግሞ ለአንድ ጊዜ ዘንቦ በመጥፋቱ ፣ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጅ ትናንት ከምሽቱ 11 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ መዝነብ የጀመረው ዝናብ እስከ 12 ሰአት ከ10 ደቂቃ ድረስ በመዝነቡ፣ የከተማው ህዝብ ደስታውን ሲገልጽ አምሽቷል።
በድርቁ ምክንያት በከተማውም ሆነ በዙሪያው ያሉት ወንዞች ድርቀዋል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታየው ድርቅ ህዝቡን እያሳሰበ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝቡ ጸሎት እያደረገ ነው።

Source :http://ethsat.com/amharic/%e1%89%a0%e1%88%b0%e1%89%86%e1%8c%a3-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%89%a3%e1%89%a2%e1%8b%8b-%e1%8a%a8%e1%8b%88%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%81%e1%8b%8b%e1%88%8b-%e1%89%b5/

No comments:

Post a Comment