ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያዊው ከአዲስ አበባ ተነስቶስ ስዊዲን ስቶኮልም አየር ማረፊያ መድረሻውን ባደረገው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው አውሮፕላን ውስጥ በዕቃ መጫኛ ውስጥ ለስምንት ሰዓታት ተደብቆ ስዊድን አራንዳ አየር ማረፊያ ገብቷል። የስዊድን ፖሊስ እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ ጣሊያን ሮም ላይ አርፎ ነበር። የአየሩ ሁኔታ በጣም ቀዝቃዛ የነበረ ቢሆንም የጤንነቱ ሁኔታ ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያለው ፖሊስ፣ የ24 ዓመቱ ወጣት የጥገኝነት ጥያቄም ማቅረቡን ገልጿል። የስዊዳቪያ አየርመንገድ ቃል አቀባይ ሄንሪ ክሌቭ ፣ ''የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ዕቃዎችን ማውረድ እንደጀመሩ ሰውዬውን አገኙት፤በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር፣ ነገር ግን ወዲያውኑ የህክምና ባለሞያዎች እንዲያዩት አድርገናል።'' ብለዋል። የስዊድን ፖሊስ አዛዥ አንድሬስ ፈርዲግስ ግለሰቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ እንደሚሰራና የያዘው መታወቂያ ወረቀቱም አብሮት እንዳለ መናገሩን አስረድተዋል። በአየር መንገዱ በነፃ የመብረር ዕድሉ እያለው ለምን በዕቃ መጫኛ ካርጎ ውስጥ ተሸሽጎ መጓዝን እንደመረጠ ፖሊስ ማጣራቱን ይቀጥላል ብለዋል። ግለሰቡ በእንስሳት ማጓጓዣ፣ ማሞቂያ ባለው ክፍል ውስጥ ተደብቆ ሳይመጣ እንዳልቀረና ይህንን ድርጊት ሊፈፅም የሚችለው ኃላፊነት ያለው ግለሰብ ብቻ መሆኑን የስዊድን ባለስልጣናት መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ስዊድን ከአውሮፓ ከጀርመን ቀጥላ ከፍተኛ ቀጥር ያለው ስደተኞችን ትቀበላለች።እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም. ውስጥ ብቻ ጥገኝነት ከጠየቁ 81,000 ኢትዮጵያዊያውን ውስጥ 35,000 ሺህ የጥገኝነት ከለላ ወረቀታቸውን አግኝተዋል። ስዊድን ውስጥ ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ የኢትዮጵያዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በ140 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
Source : http://ethsat.com/amharic/%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%8d%e1%88%ae%e1%8d%95%e1%88%8b%e1%8a%91-%e1%89%a0%e1%8b%95%e1%89%83-%e1%88%98%e1%8c%ab/
"Democracy must be built through open societies that share information" Atifete Jahjaga
Press Freedom, Democracy and Human right
Friday, August 14, 2015
አንድ ኢትዮጵያዊ በአውሮፕላኑ በዕቃ መጫኛ ክፍል ውስጥ ተደብቆ ስዊድን ገባ
Labels:
Amharic News,
Ethiopia
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment