ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነሃሴ 7 ፣ 2007 በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ አድማ በታኝ ፖሊስ በአካባቢው የሰፈረ ሲሆን፣ ውጥረቱ አሁንም ድረስ መኖሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ በሚታሰበው ቦታ አካባቢ ዛሬም ግጭት እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። በትናንቱ ግጭት የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ፣ ሌሎች አመራችም የተደበደቡ ሲሆን፣ እስካሁን 2 ሰዎች መሞታቸውና 2 ፖሊሶች ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል። አብዛኞቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሁለተኛ ቀን ተዘግተው ውለዋል። የተቃውሞው መንስኤ በወረዳው ሊገነባ የነበረው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ወደ መካነ ሰላም መዛወሩን ተከትሎ ነው። የብአዴን ሊ/መንበርና ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከምርጫ በፊት ወደ አካባቢው በመሄድ የዩኒቨርስቲውን የመሰረት ድንጋይ ቢያስቀምጡም፣ ከምርጫው በሁዋላ ውሳኔው ተሽሮ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለተቃውሞ አስነስቷቸዋል።
Source : http://ethsat.com/amharic/%e1%89%a0%e1%88%88%e1%8c%8b%e1%88%9d%e1%89%a3-%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%89%b3%e1%8b%a8%e1%8b%8d-%e1%8b%8d%e1%8c%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%89%80/
"Democracy must be built through open societies that share information" Atifete Jahjaga
Press Freedom, Democracy and Human right
Friday, August 14, 2015
በለጋምባ ወረዳ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው
Labels:
Amharic News,
Ethiopia
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment